በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኮሮናቫይረስ ክትባት ለማግኘት የሚደረግ ጥረት


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

የብሪታንያ የጤና ጉዳይ ተቆጣጣሪዎች፣ የኮሮናቫይረስ ክትባት ለማግኘት በሚደረድገው ጥረት፣ የጥናቱን ሂደት ግምገማ ማፋጠን መጀመራቸውን ትናንት አስታውቀዋል።

“የመድሀኒትና የጤና ጥበቃ ምርቶች ተቆጣጣሪ አገልግሎት፣ የኮቪድ-19 ክትባት ሙከራችን ላይ የሚያደርገውን ግምገማ ማፋጠን መጀመሩን እናረጋግጣለን ሲል፣ የአስታራዘኒካ ቃል አቀባይ ተናግሯል።

የግምገማው ሂደት ሲፋጠን፣ ተቆጣጣሪዎቹ የክትባት መድሃኒቱን የማጽደቅ ሂድትን ለማፋጠን ሲሉ፣ ክትባቱ በተግባር ላይ ሲውል የመመልከትና ስለ ክትባቱ የአመራረት ሂደት የመመልከትና ከአምራቾቹ ጋር የመነጋገር ተግባር ያካሄዳሉ።

አስቸኳይ የጤና ሁኔታ ሲኖር፣ የመድሃኒትነትና የክትባትነት ተስፋ ያለው ሁኔታ ሲፈጠር፣ ሂደቱ ከተለመደው በላይ እንዲፋጠን የሚጠቀሙበት ዘዴ መሆኑ ታውቋል።

አስትራዘኒካና ፕፊዘር የኮሮናቫይረስ የክትባት መድሃኒት ለማግኘት በሚደረገው መረባረብ፣ የቅድሚያ ቦታ ከያዙት መካከል መሆናቸው ተገልጿል። ጆንሰን ኤንድ ጆንሰንና ሞደርና ኩባንያዎችም፣ የክትባት መድሃኒቱን ለመስራት እየተጣደፉ ከሚገኙት፣ የመድሃኒት ኩባንያዎች መካከል ናቸው።

የብሪታንያው የመድሃኒት ኩባንያ፣ ዛሬ በተናገረው መሰርት፣ የኮቪድ-19ኙ የሙከራ ክትባት፣ በዕድሜ በገፉትና በወጣቶች ላይ የመከላከል ብቃት አሳይቷል።

እስካሁን ባለው ጊዜ፣ በዓለም ደረጃ 1.19 ሚልዮን የሚሆኑ ሰዎች፣ በቫይረሱ ተይዘው ለሞት ተዳርገዋል። የሀገራትን ኢኮኖሚ አዳሽቋል። በቢልዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች የኑሮ ሁኔታን አተራምሷል።

XS
SM
MD
LG