በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቴሬሣ ሜይ ከሥልጣን ለማውረድ ከተደረገባቸው ሙከራ ተረፉ


ፎቶ ፋይል፡- የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ቴሬሣ ሜይ
ፎቶ ፋይል፡- የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ቴሬሣ ሜይ

የእንግሊዟ ጠቅላይ ሚኒስትር ቴሬሣ ሜይ የራሣቸው ወግ አጥባቂ ተቺዎች ከሥልጣን ለማውረድ ካደረጉባቸው ሙከራ ተርፈዋል።

የእንግሊዟ ጠቅላይ ሚኒስትር ቴሬሣ ሜይ የራሣቸው ወግ አጥባቂ ተቺዎች ከሥልጣን ለማውረድ ካደረጉባቸው ሙከራ ተርፈዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው እንዲቀጥሉ የሚያስችላቸውን የመተማመኛ ድምፅ አግኝተዋል። ወግ አጥባቂ የፓርላማ አባላቱ ቴሬሳ ሜይ ብሪታኒያ ከአውሮፓ ህብረት አባልነት ለመውጣት የምታደርገውን የፍቺ ድርድር የያዙበት መንገድ እንዳላስደሰታቸው ይነገራል።

ትላንት ማታ በሚስጥር በተካሄደው የድምፅ መስጠት ሥነ ስርዓት ቴሬሣ ሜይ ከ317 ወግ አጥባቂ የፓርላማ አባላት 2መቶ የሚሆኑትን ሲያገኙ፣ 117 የሚሆኑ ተቃውመዋቸዋል።

ሜይ ከመተማመኛ ድምፁ በኋላ ለተደረገላቸው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።

ብሪታኒያ ከአውሮፓ ህብረት ለመውጣት በያዘችው የፍቺ ድርድር በርካታ የሀገሪቱ ዜጎች ሥጋት እንደገባቸው መረጃዎች ያመለክታሉ።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG