በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቦሪስ ጆንሰን በኮቪድ ምላሽ ጉዳይ ቃላቸውን ሰጡ


የቀድሞው የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን
የቀድሞው የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን

የቀድሞው የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ስለጠፋው የሰው ህይወት መፀፀታቸውን ገለፁ።

ጆንሰን በኮቪድ 19 ሰዎች “ለስቃይ፡ ለሞት እና ለሐዘን በመዳረጋቸው አዝናለሁ” ብለዋል፡፡

የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር ይሕንን ያሉት በሀገሪቱ ከ230,000 በላይ ሰዎችን ለገደለው እና ሀገሪቱ ለቀውሱ የሰጠችውን ምላሽ በሚመረምረው ቡድን ፊት ቀርበው ለሁለት ቀናት የሚሰጡትን ቃል ሲጀምሩ ነው፡፡

በእንግሊዝ በኮቪድ 19 ምክንያት የሞቱት ሰዎች ቁጥር አውሮፓ ውስጥ ከተመዘገቡ ከፍተኛ የሟቾች ቁጥር አንዱ ነው፡፡

ቦሪስ ጆንሰን የተቃውሞ ሰልፍ የሚያደርጉ የኮቪድ 19 ሰለባዎች ቤተሰቦች እንዳያገኟቸው ብለው ምርመራው ሥፍራ የገቡት ጎህ ሳይቀድ ነበር፡፡

የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር እኤአ በ2019 ስልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት የተከሰተው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ አያያዛቸው ብርቱ ነቀፌታ አስከትሎባቸዋል፡፡

እሳቸው እና ሠራተኞቻቸው የመንግሥትን የስብሰባ ክልከላዎች ችላ ብለው በጠቅላይ ሚኒስትሩ ኦፊሴላዊ መኖሪያ ቤት ድግስ ሲደግሱ እንደነበር ከታወቀ እና ሌሎችም መሰል ቅሌቶች መከሰታቸውን ተከትሎ ከሶስት ዓመታት የሥልጣን ቆይታ በኋላ፣ እ.ኤ.አ. በ2022 ከሠራተኞቻቸው ጋር ከሥልጣናቸው እንዲለቅቁ መገደዳቸው ይታወሳል፡፡

የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መንግሥታቸው “አንዳንድ ነገሮችን እንደተሳሳተ” አምነው፣ ሆኖም በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ የተቻላቸውን ሁሉ እንደሠሩ ተናግረዋል።

በርካታ የቀድሞ ባለስልጣናት እና ረዳቶቻቸው በሰጡት የምስክርነት ቃል ጆንሰንን ወላዋይ እና ለተጎጂዎች የሚራራ አንጀት ያልነበራቸው አድርገው አቅርበዋቸዋል፡፡ “በዕድሜ የገፉ ብሪታንያውያን ቢሞቱስ” ይሉ እንደነበር እና የንግድና ማህበራዊ ተቋማትን ለሁለተኛ ጊዜ ከመዝጋት ብዙ ሰው ቢሞት ይሻላል” ይሉ ነበር ሲሉ የምስክርነት ቃል የሰጡም አሉ፡፡

የጠቅላይ ሚንስትር ቦሪስ ጆንሰን የሳይንስ ጉዳይ አማካሪያቸው የነበሩት ፓትሪክ ቫላንስ ኮቪድን በሚመለከተው ሳይንስ “ግራ ይጋቡ” ነበር ብለዋቸዋል፡፡ ሌላው የቀድሞ አማካሪያቸው ዴቪድ ከሚንግስ ደግሞ ቦሪስ በአንድ ወቅት “አፍንጫዬ ውስጥ የጸጉር ማድረቂያ ብለቅቅበት ቫይረሱን አይገድለውም?” ብለው ሳይንቲስቶችን ጠይቀው እንደነበር ተናግረዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG