በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጄነራል ለገሠ ተፈራ አረፉ


ብሪጋዲየር ጄነራል ለገሠ ተፈራ
ብሪጋዲየር ጄነራል ለገሠ ተፈራ

የኅብረተሰብዓዊት ኢትዮጵያ ጀግና ሜዳይ ተሸላሚ የነበሩት ብሪጋዲየር ጄነራል ተፈራ ለገሠ ዛሬ አረፉ፡፡

የኅብረተሰብዓዊት ኢትዮጵያ ጀግና ሜዳይ ተሸላሚ የነበሩት ብሪጋዲየር ጄነራል ተፈራ ለገሠ ዛሬ አረፉ፡፡

ብሪጋዲየር ጄነራል ለገሠ አሜሪካ ውስጥ በሕክምና ሲረዱ መቆየታቸውን ለቤተሰቡ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡

ብ/ጄነራል ለገሠ ተፈራ ከሃረር የጦር አካዳሚ በ1959 ዓ.ም ተመርቀው የኢትዮጵያ አየር ኃይልን መቀላቀላቀላቸውንና የጄት አብራሪና መምህር ሆነው ማገልገላቸውን የሕይወታቸው ታሪክ ይናገራል፡፡

የዚያድ ባሬ ሶማሊያ ጦር በ1960ዎቹ መጨረሻ ኢትዮጵያን በምሥራቅና በደበቡብ ምሥራቅ በኩል ወርሮ በነበረ ጊዜ የዘጠነኛው ስኳድሮን ባልደረባ የነበሩት ተዋጊ ጄት አብራሪ ጄነራል ለገሠ ተፈራ አምስት የሶማሊያ ጦር አይሮፕላኖችን በአየር ላይ ውጊያ መትተው መጣላቸው ይነገርላቸዋል፡፡

ጄነራል ለገሠ ተፈራ በጦር እሥረኛነት ለአሥራ አንድ ዓመታት ሶማሊያ ውስጥ ከቆዩ በኋላ ወደ ሃገራቸው ሲገቡ ወደ ኢትዮጵያ አየር ኃይል ተመልሰው በበረራ አስተማሪነት አገልግለዋል፡፡

ግንባር ላይ ለፈፀሙት ጀብዱም የጦር ሜዳ ጀብዱ ሜዳይና የኅብረተሰብዓዊት ኢትዮጵያ ጀግና ሜዳይ በወቅቱ የኢትዮጵያ መሪ ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም ተጠልቆላቸዋል፡፡

ብሪጋዲየር ለገሠ ተፈራ ኮ/ል መንግሥቱ ኃይለማርያምን ከሥልጣን ለመገልበጥ የተሞከረው የ1983ቱ ኩዴታ ሲከሽፍ ወደ አሜሪካ ተሰድደው እስከ ሕልፈታቸው እዚያው ኖረዋል፡፡

ብሪጋዲየር ለገሠ ተፈራ ሦስት ልጆችን አፍርተዋል፡፡

ብሪጋዲየር ጄነራል ለገሠ ተፈራ
ብሪጋዲየር ጄነራል ለገሠ ተፈራ

XS
SM
MD
LG