በአሜሪካ ካልፎርኒያ ግዛት ውስጥ አንድ አነስተኛ አውሮፕላን ትላንት ሐሙስ ተከስክሶ ሁለት ሰዎች ሕይወታቸውን እንዳጡ ፖሊስ አስታውቋል።
አውሮፕላኑ ደቡብ ካልፎርኒያ ውስጥ በሚገኘ አንድ የቤት ዕቃዎች ማምረቻ መጋዘን ላይ እንደተከሰከሰም ፖሊስ አስታውቋል።
የአውሮፕላኑ መከስከስ እሳት በማስነሳቱም 200 የሚኾኑ ሠራተኞች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ተደርጓል። ዐስራ አንድ በሚኾኑ ሰዎች ላይ ጉዳት በመድረሱ ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል። ሌሎች ስምንት የሚሆኑት በሥፍራው ሳሉ የሕክምና ርዳታ ተደርጎላቸዋል።
በአደጋው ሕይወታቸው ያለፈው ሰዎች በአውሮፕላን ውስጥ የነበሩት እንደሆነ ተገምቷል።
የፌዴራሉ አቪዬሽን አስተዳደር ምርመራ በማድረግ ላይ መሆኑን አስታውቋል።
መድረክ / ፎረም