በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በእሳት የጋየው የብራዚል ብሄራዊ ቤተ መዘክር

ትላንት በእሳት ጋይቶ ከወደመው የብራዚል ብሄራዊ ቤተ መዘክር የተረፈ ነገር ካለ ለማየት የእሳት አደጋ ሰራተኞች እየፈለጉ ናቸው። የማይተኩ የሀገሪቱን ታሪክ የሚያንፀባርቁ ሰፊ ይዘት የነበራቸው የቅርሳቅርስ ስብስቦች በነው በመቅረታቸው የሀገሪቱ ህዝብ ከፍተኛ ሀዘን እንደተሰማው ተገልጿል።

ትላንት በእሳት ጋይቶ ከወደመው የብራዚል ብሄራዊ ቤተ መዘክር የተረፈ ነገር ካለ ለማየት የእሳት አደጋ ሰራተኞች እየፈለጉ ናቸው። የማይተኩ የሀገሪቱን ታሪክ የሚያንፀባርቁ ሰፊ ይዘት የነበራቸው የቅርሳቅርስ ስብስቦች በነው በመቅረታቸው የሀገሪቱ ህዝብ ከፍተኛ ሀዘን እንደተሰማው ተገልጿል።

የ2መቶ ዓመታት ዕድሜ ያለው ቤተመዘክር በአሜሪካ ሀገሮች ባልታየ መልኩ ረዥም ዕድሜ ያለው የሰው ቅሪት አካልን የመሳሰሉ፣ ብራዚል ውስጥ ከተገኙት ትልቁ የሆነ /Meteorite/ የታሪክ ማስታወሻዎች፣ የአንትሮፖሊጂና ሌሎችም በርካታ ቅርሶችን የያዘ እንዳነበር ታውቋል።

ሪዮ ዴ ጄኔሮ ውስጥ የስዎች የሀዘን ስሜት ወደ ቁጣ ተቀይሮ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በቤተ መዘክር አካባቢ ተሰባስበው የደረሰውን ጉዳት ለማየት ቢጠይቁም ታግደዋል። አንዳንዶቹ ገፍተው ለመግባት ሞክረዋል፣ ሆኖም ፖሊሶች ዕምባ አስመጪ ጋዝ በመተኮስና በቆመጥ መለስዋቸዋል።

በእሳት የጋየው የብራዚል ብሄራዊ ቤተ መዘክር
please wait

No media source currently available

0:00 0:00:36 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG