በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የብራዚል ጽንፈኛ ቀኝ ዘመም ፕሬዚዳንት የፈረንሳዩ አቻቸውን ነቀፉ


የብራዚል ጽንፈኛ ቀኝ ዘመም ፕሬዚዳንት ጃረ ቦለሶንሮ የፈረንሳዩን አቻቸው “ከቀኝ ገዢነት አመለካከት” አልወጡም ሲሉ ነቅፈዋል።

የአማዞን ሰደድ እሳት ጉዳይ ቡድን ሰባት የሚባሉት በኢንዱስትሪ የበለፀጉት ሀገሮች ጉባዔ ላይ፣ ቀዳሚ ቦታ መያዝ አለበት በማለታቸው ነው የብራዚሉ ፕሬዚዳንት የተቆጡት።

"የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት የአማዞኑ ሰደድ እሳት ጉዳይ የሚመለካተቸው ሀገሮች በማይስተፉባት የቡድን ሰባት ጉባዔ ላይ ውይይት እንዲከፈትባት መጠየቃቸው በ21ኛው ምዕታ ዓመት ቦታ የማያገኘውን የቅኝ ገዥነት አመለካከትን ያስታውሰናል" ሲሉ የብራዚሉ ፕሬዚዳንት ትናንት በትዊተር አስተላልፈዋ።

ሀገሮች ስለ አማዞን ጉዳይ ለብራዚል ገንዘብ የሚልኩት ለመርዳት ብለው ሳይሆን በሉዓላዊነታችን ላይ ጣልቃ ለመግባት ነው ብለዋል ፕሬዚዳንቱ።

የአማዞን ደንን እያጋየ ያለው ሰደድ እሳት ወሳኝና የማይተካ ሰፊ ብዘሃ ህይወትን የማጥፋት አደጋ ደቅኗል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG