በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቦትስዋና የተመሳሳይ ፆታ ፍቅረኝነት ወንጀል እንዳይሆን ወስነች


ቦትስዋና የተመሳሳይ ፆታ ፍቅረኝነት ወንጀል እንዳይሆን ወስናለች። ከሰሀራ በመለስ ያሉት በርካታ ሃገሮች የተመሳሳይ ፆታዎች ወሲብ ወንጀል እንዲሆን የሚያደርጉ ህጎች አሏቸው።

የቦትስዋና ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተመሳሳይ ፆታዎች መካከል የሚደረግ ወሲብን እስከ ሰባት ዓመታት ድረስ የሚያሳስረው ሁለት ክፍል ያለው የወንጀለኛ መቅጭ ህግ ህጋዊ አይደለም የሚል ብይን ሰጥቷል።

የከፍተኛው ፍርድ ቤት ዳኛ ማይክል ኤልቡሩ አብዛኞቹ ህጎች ከቅኝ ግዛቱ ወቅት አንስቶ የነበሩ ሲሆኑ የሀገሪቱን ውሁዳን ህዝቦችን የሚጨቁኑ ናቸው ብለዋል። ፍርድ ቤቱን ሞልተው የነብሩት አክቲቪስቶች በደስታ ፈንድቀዋል።

ፍርድ ቤቱ በጉዳዩ ላይ ዕርምጃ እንዲውስድ ፊርማዎችን አሰባስበው ያቀረቡት ሰው ለደኅንነታቸው ሲባል ስማቸው አልተገለጸም።

የኬንያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተመሳሳይ ፆታ ወሲብን በወንጀል ደረጃ የሚደነግገውን ህግ ባለፈው ወር ባፀደቀበት ወቅት አክቲቪስቶች አዝነው ነበር። ከቦትስዋናው ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔ በፊት ከሰሀረ በመለስ ካሉት 49 ሀገሮች መካከል 28ንቱ የተመሳሳይ ፆታ ግንኑነትን ወንጀል የሚያደርጉ ህጎች አሏቸው፡፡

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG