በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ወረባቦ ላይ ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸው ተዘገበ


የኢትዮጵያ መንግሥት በአሸባሪነት የፈረጀው የህወሓት ታጣቂዎች ደቡብ ወሎ ዞን ወረባቦ ወረዳ ውስጥ በቆዩባቸው ቀናት “ሰላማዊ ሰዎችን በወል ግድለዋል” ሲሉ የአካባቢው ባለሥልጣናት ተናግረዋል።

በሌላ በኩል የህወሓት ቃል አቀባይ ታጣቂዎቹ በሚወነጀሉበት በዚህ ክስ ወዲያኑ ማስተባበያ ባይሰጡም ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ ሰላማዊ ሰዎችን በመግደል የሚቀርብባቸውን ውንጀላ፤ ተዋጊዎቻችን ሲቪሎችን ገድለዋል የሚለውን ውንጀላ አጥብቀን እናስተባብላለን ማለታቸው ይታወሳል።

በሌላ በኩል ደሴ የሚገኘው ዘጋቢያችን በፀጥታ ችግር ምክንያት ወደ አካባቢው መጠጋትና በስልክና የኢንተርኔት ግንኙነት ችግር ምክኒያት ተጨማሪ መረጃዎችን ማግኘት እንዳልቻለ ጠቅሶ የቤተሰቦቻቸው አባላት እንደተገደሉባቸው የገለፁ በስፍራው ለተገኙ የአገር ውስጥ ጋዜጠኞች የሰጡን የድምፅ አስተያየት ታማኝ ከሆኑ ምንጮቹ እንዳገኘው ከጠቆመው በምስል የተደገፈ መረጃ ጋር አካትቶ ዘግቧል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

ወረባቦ ላይ ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸው ተዘገበ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:44 0:00


XS
SM
MD
LG