በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአውሮፓ ኅብረት አገራት ለዩክሬን የመድፍ ጥይት ሊሰጡ ተስማሙ


የአውሮፓ ኅብረት የውጪ ጉዳይ ፖሊሲ ኃላፊ ጆሴፕ ቦረል
የአውሮፓ ኅብረት የውጪ ጉዳይ ፖሊሲ ኃላፊ ጆሴፕ ቦረል

የአውሮፓ ኅብረት አገራት ለዩክሬን እጅግ አስፈላጊ የሆነውን የመድፍ ጥይት በአስቸኳይ ለመስጠት አንደተስማሙ የኅብረቱ የውጪ ጉዳይ ፖሊሲ ኃላፊ ጆሴፕ ቦረል ትናንት አስታውቀዋል።

ብራስልስ ላይ ከህብረት አገራቱ የውጪ ጉዳይና የመከላከያ ሚኒስትሮች ጋር ከመከሩ በኋላ ቦረል በሠጡት መግለጫ፣ ሥምምነቱ ዩክሬን ራሷን የመከላከል መብቷን በተመለከተ የኅብረቱ አገራት ከጉኗ እንደቆሙ ግልጽ ማስረጃ ነው ብለዋል።

በሩሲያው ፕሬዚዳንት ላይ በዓለም አቀፉ የጦር ወንጀል ፍ/ቤት የወጣው የማዘዣ ትዕዛዝን አስመልክቶ ቦረል ሲናገሩም፣ በዩክሬን ላይ በተፈጸመው ሰቆቃ የሩሲያ መሪዎችን ተጠያቂ ማድረግን በተመለከተ ቀድመን በተደጋጋሚ ግልጽ አድርገናል ብለዋል።

የእሥር ማዘዥ ትዕዛዙ ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጋር ያላቸውን ግንኙነት በተመለከተ ፑቲንን አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ይከታቸዋል ብለዋል ቦረል።

ቦረል በተጨማሪም ቱኒዚያ ውስጥ ያለው ሁኔታ ሌላው የስብሰባው ትኩረት እንደነበር አውስተዋል።

የቱኒዚያው ፕሬዚዳንት ካይስ ሳይድ ከሰሃራ ግርጌ ካሉ አገሮች በሚመጡ ስደተኞች ላይ እርምጃ እንዲወሰድ አዘዋል። በጥቁሮች ላይ ያነጣጠረ የዘረኝነት እርምጃ ነው የሚል ክስ ቢቀርብባቸውም ካይስ ያስተባብላሉ።

XS
SM
MD
LG