ዋሺንግተን ዲሲ —
ቦሪስ ጆንሰን ሰኞ ማታ በተካሄደው የመጀጨረሻ ውድድር፤ ተፎካካሪያቸው የነበሩትን ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ጀርሚ ሀንትን በቀላሉ 66% ለ34% በሆነ ብልጫ ነው ያሸነፏቸው።
ባደረጉትም የድል አድራጊነት ንግግር፣ ብሪታንያ እአአ በጥቅምት 31 ከአውሮፓ ሕብረት የምትወጣበትን ቀላል ሁኔታ እንደሚያመቻቹ ጠቁመው፣ የትምህርቱን፣ የመሠረተ ልማቱንና የፖሊሱን ክፍል ለማሻሻል ሀገራቸው የምታደርጋቸውን ጥረቶች እንደሚያግዙ አመልክተዋል።