በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቦረና ተቸግሯል፤ ግን አልተራበም


ድርቅ ያፈናቀላቸው የቦረና ከብት አርቢዎች በጉዞ ላይ
ድርቅ ያፈናቀላቸው የቦረና ከብት አርቢዎች በጉዞ ላይ

ያልተራበው ሃምሣ ከመቶ የሚጠጋው ህዝብ እርዳታ ማግኘት በመቻሉ ነው።

የቦረና ከፊል አርሦአደሮች የመጭውን የምርት ዘመን ዘራቸውን ፈልፍለው በመብላት ላይ ናቸው። አርብቶ አደሮቹ ከሰባ ከመቶ በላይ የሚሆኑ የሁሉም ሕይወታቸው መሠረት የሆኑ ከብቶቻቸው አልቀውባቸዋል፡፡

ለወትሮ አነሰ ቢባል ሰላሣ፣ ሲኖረውም እስከ መቶ ሃምሣ ራስ መንጋ የነበረው ዛሬ ግና ሁለት፣ ግፋ ቢል እስከ አሥራ አምስት ከብቶች ያሉት የሚበዛው አርብቶ አደር እነርሱኑ ነድቶ ወደ ኮንሶና ዳመና ወደሚታይባቸው ያቤሎና አካባቢው አምርቷል።

ሄኖክ ድርቅ በየቦታው የጣላቸውን የቦረና ከብቶች አጥንት ፎቶ ያነሣል

በአካባቢው ለሁለት ዓመታት ዝናብ ሣይጥል ቆይቶ የዘነበው የከበደ ዝናብ የአካባቢውን ኩሬዎች ጠራርጎ የወሰደ ጎርፍ በማስከተሉ የውኃ እጥረት ችግሩን ይበልጥ አባብሶታል፡፡ ድርቁ፣ የውኃውም እጥረት ስፋት ያላቸውን አካባቢዎች ለረሃብ አጋልጧል፡፡

ዘጋቢያችን ሔኖክ ሰማእግዜር በአካባቢው ተዘዋውሮ ባጠናቀረው ዘገባ መሠረት የመስከረም አጋማሹ ዝናብ ካልዘነበ የከፋ ረሃብና ሰብዓዊ እልቂት ሊኖር ይችላል።

ዝርዝሩን ያዳምጡ፡፡

ተመሳሳይ ርእስ

XS
SM
MD
LG