በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በድንበር ጠባቂዎች ተይዛ የነበረችው ሜክሲኮያዊት ሕፃን ሕይወቷ አለፈ

ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

ባለፈው ሣምንት ከአባቷ ጋር ከሜክሲኮ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ያለ ፈቃድ ስታቋርጥ በድንበር ጠባቂ ዘቦች ተይዛ የታሠረችው የ7 ዓመት ሕፃን ሕይወቷ ማለፉን፣ የፌዴራሉ የፍልሰተኞች ጉዳይ ባለሥልጣናት አረጋገጡ።

ባለፈው ሣምንት ከአባቷ ጋር ከሜክሲኮ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ያለ ፈቃድ ስታቋርጥ በድንበር ጠባቂ ዘቦች ተይዛ የታሠረችው የ7 ዓመት ሕፃን ሕይወቷ ማለፉን፣ የፌዴራሉ የፍልሰተኞች ጉዳይ ባለሥልጣናት አረጋገጡ።

በዋሺንግተን ፖስት ጋዜጣ ዘገባ መሠረት፣ ልጂቱ ሎርድስበርግ ኒው ሜክሲኮ ውስጥ ከተያዘች ከሰዓት በኋላ ለሕልፈት የበቃችው፣ በውሃ ጥም እና ድንጋጤ ሳቢያ ነው።

የጓቴማላ ዜግነት ያላት ልጅ ከአንድ ሣምንት በፊት ትጓዝ የነበረው ከሌሎች 163 ሰዎች ጋር እንደነበርም ተዘግቧል።

የዩናይትድ ስቴትስ ያገር ውስጥ ደኅንነት መሥሪያ ቤት እንደገለጸው፣ ልጅቱ በድንበር ቃኚዎች እጅ በነበረችበት ወቅት በከባዱ ያንቀጠቅጣት እንደነበርና በመሥሪያ ቤቱ የጤና ወኪል ምርመር ሲደረግላትም፣ የሰውነቷ ትኩሳት መጠን 41 ዲግሪ ሴልሲየስ ደርሷል። ወዲያው በአውሮፕላን ወደ ኤልፓሦ ቴክሳስ የተወሰደችው ሕጻን 24 ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የልብ ትርታዋ ቆሞ ለሕልፈት በቅታለች ተብሏል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG