አዲስ አበባ —
ካለፈው ሰኔ ጀምሮ ሲያካሂድ የቆየውን የዳሰሳ ጥናት የፊታችን ግንቦት እንደሚያጠናቅቅና ምክረ ሐሳብም እንደሚያቀርብ የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን አስታወቀ።
ለፌዴሬሽን ምክር ቤት የሚቀርበውም አንተም ተው፣ አንችም ተይ ዓይነት መፍትሔ ሳይሆን በጥናት ላይ የተመሰረተ ምክረ ሐሳብ ነው ብለዋል የኮሚሽኑ ፅ/ቤት ዳይሬክተር አወል ሁሴን።
ከአስተዳደር ወሰን እና ከማንነት ጋር በተያያዘ ለሚፈጠሩ ግጭቶች የመጨረሻ እልባት ለመስጠት እንዲያስችል ነው ኮሚሽኑ በየካቲት 2011 በአዋጅ የተቋቋመው።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡