በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቦምብ በማፈንዳት ከተጠረጠሩ በአምስቱ ላይ ክስ ሊመሰረት ነው

ለኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ድጋፍ ለመስጠት ሰኔ 16 ቀን 2010 ዓ.ም በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ በተዘጋጀ ሰልፍ ላይ ቦምብ በማፈንዳት ከተጠረጠሩ ግለሰቦች መካከል በአምስቱ ላይ ክስ ሊመሰረት መሆኑ ተገለፀ፡፡

ለኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ድጋፍ ለመስጠት ሰኔ 16 ቀን 2010 ዓ.ም በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ በተዘጋጀ ሰልፍ ላይ ቦምብ በማፈንዳት ከተጠረጠሩ ግለሰቦች መካከል በአምስቱ ላይ ክስ ሊመሰረት መሆኑ ተገለፀ፡፡

አብዲሳ ቀነኔ፣ ደሳለኝ ተስፋዬ፣ ጌቱ ግርማ፣ ህይወት ገዳ እና ባህሩ ቶላ በተባሉት ተጠርጣሪዎች ላይ መርማሪ ፖሊስ ምርመራውን አጠናቆ መዝገቡን ለአቃቤ ህግ ማስረከባቸውን መንግሥታዊ የዜና ማሰራጫ ፋና ዘግቧል፡፡

አቃቤ ህግ ፍርድ ቤቱ ክሱን ለመመስረት የአሥራ አምስት ቀን ጊዜ እንዲሰጣቸው ያቀረቡትን ጥያቄ ተቀብሏል። የተጠርጣሪዎቹን የዋስ መብት ጥያቄ ውድቅ አድርጎ በማረፊያ ቤት እንዲቆዩ አዟል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አሕመድ በአዲስ አበባው የድጋፍ ሰልፍ ላይ ንግግር አድርገው እንዳበቁ በደረሰው ፍንዳታ ሁለት ሰዎች ሲገደሉ ከአንድ መቶ ሃምሳ የሚበልጡ ሌሎች መቁሰላቸው አይዘነጋም።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG