በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዲሞክራቲክ ኮንጎ ቤተ ክርስቲያን ላይ የቦምብ ፍንዳታ 10 ሰዎች ገደለ


ኮንጎ ዲሞክራሲያዊት ኮንጎ ሪፐብሊክ ውስጥ በሚገኝ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በደረሰ የቦምብ ፍንዳታ ቢያንስ 10 ሰዎች ሲገደሉ ሌሎች 39 ሰዎች መቁሰላቸው ተዘግቧል።

አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደዘገበው ጥቃቱን ያደረሱት እስልምና አክራሪዎች ናቸው የሚል ጥርጣሬ አለ።

የኮንጎ ወታደራዊ ቃል አቀባይ በሰጡት መግለጫ ከዩጋንዳ ጋር በሚያዋስነው የሰሜን ኪቩ ካሲንዲ ከተማ በሚገኝ ቤተ ክርስቲያን ላይ የአሸባሪ ጥቃት ተፈጽሟል ማለታቸውን ዘገባው ጠቅሷል።

በኮንጎ የዩጋንዳ ወታደራዊ እንቅስቃሴ ቃል አቀባይ በበኩላቸው በጥቃቱ አስራ ስድስት ሰዎች እንደተገደሉ እና ሃያ ሰዎች እንደቆሰሉ መናገራቸውን ዘገባው አመልክቷል። ጥቃቱን ያደረሰው የተባበሩት ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች (ኤዲኤፍ) ነው ብለን እንጠረጥራለን ብለዋል።

የኮንጎ የኮሙኒኬሽን ሚኒስቴርም ጥቃቱን ያደረሰው ኤዲኤፍ ነው ብሏል። ታጣቂውን ቡድን ራሱን እስላማዊ መንግሥት ብሎ የሚጠራው ቡድን የማዕከላዊ አፍሪካ ቅርንጫፉ መሆኑን ተናግሯል።

XS
SM
MD
LG