በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በቦሊቪያ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ከሸፈ

በቦሊቪያ ትላንት ረቡዕ ለአጭር ሰዓታት የቆየውና በሃገሪቱ ሠራዊት አዛዥ ዃ ሆሴ ሱኒጋ የተመራ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ መክሸፉ ተነግሯል።
በቦሊቪያ ትላንት ረቡዕ ለአጭር ሰዓታት የቆየውና በሃገሪቱ ሠራዊት አዛዥ ዃ ሆሴ ሱኒጋ የተመራ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ መክሸፉ ተነግሯል።

በቦሊቪያ ትላንት ረቡዕ ለአጭር ሰዓታት የቆየውና በሃገሪቱ ሠራዊት አዛዥ ዃ ሆሴ ሱኒጋ የተመራ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ መክሸፉ ተነግሯል።

በሱኒጋ የተመሩት ወታደሮች የፕሬዝደንት ሉዊስ አርሴ ቤተመንግስትን በታንክ ገርስሰው ከገቡና በመዲናዋ የሚገኘውን ዋና አደባባይ ከተቆጣጠሩ በኋላ፣ ፕሬዝደንቱ ሌላ አዛዥ በመሾም ሁኔታውን መቆጣጠራቸው ተዘግቧል።

መፈንቅለ መንግስቱን ያቀነባበሩትና ትዕዛዝም የሰጡት ፕሬዝደንቱ እራሳቸው እንደሆኑ እና ተወዳጅነታቸውና ድጋፋቸ እንዲጨምር ሆን ብለው ያደረጉት እንደሆነ ጀኔራል ዃ ሆሴ ሱኒጋ ከመያዛቸው በፊት ተናግረዋል። ተቃዋሚ እንደራሴዎችና የመንግስት ነቃፊዎችም የጀኔራሉን ውንጀላ ደግፈው ተናግረዋል። “በራስ ላይ የተፈጸመ የመንግስት ግልበጣ ሙከራ” ሲሉ ገልጸውታል።

ዛሬ ሐሙስ ፕሬዝደንት ሉዊስ አርሴን የሚደግፉ ቦሊቪያውያን በቤተመንግስቱ ተሰባስበው የመፈንቅለ መንግስት ሙከራውን ሲያወግዙና ለፕሬዝደንቱ ያላቸውን ድጋፍ ሲገልጹ ተስተውለዋል።

ፕሬዝደንት ሉዊስ አርሴ የመንግስት ግልበጣ ሙከራ ከተባለው ክስተት ወዲህ ያገኙት የሕዝብ ድጋፍ ጊዜያዊ ቢሆንም፣ ከቀድሞ አጋራቸውና አሁን ደግሞ የፖለቲካ ባላንጣቸው ከሆኑት የቀድሞው ፕሬዝደንት ኢቮ ሞራለስ ጋራ በመጪው ዓመት ላለባቸው የምርጫ ፉክክር ጠቃሚ ሊሆን እንደሚችል ተንታኞች ተናግረዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG