ዋሺንግተን ዲሲ —
ከዘጠና በላይ የሚሆኑ ናይጀርያውያን ሴት ተማሪዎች ፅንፈኞቹ የቦኮ ሐራም አማፅያን በሰሜን ምስራቅ ዮቤ ክፍለ ሀገር የሚገኘውን ትምህርት ቤታቸውን ከሁለት ቀናት በፊት ካጠቁ በኋላ የገቡበት እንዳልታወቀ ተገልጿል።
ስለጉዳዩ በቅርብ የሚያቁ ሰዎች እንደሚሉት ትምህርት ቤቱ ትላንት ሲከፈት 91 ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት አልገቡም። ይህ ክስተት ታድያ ቦኮ ሐራም አሁንም የገፍ ጠለፋ ሳያካሄድ አልቀረም የሚል ስጋት አሳድሯል።
ቦኮ ሐራም ከሁለት ዕእመታት በፊት ሚያዝያ ወር ላይ 276 የሚሆኑ ተማሪ ሴቶችን ቺቦክ በተባለው ገጠር ከሚገኘው ትምህርት ቤታቸው መጥለፉ የሚታወስ ነው።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ