በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ ዓየር መንገድ አውሮፕላን አደጋ መንስዔ ፍለጋና ጥያቄዎቹ


የኢትዮጵያ ዓየር መንገድ አውሮፕላን አደጋ፣ የኒው ዮርክ ታይምስ ዘገባ፣ ቦይንግና የዩናይትድ ስቴትሱ የፌዴራል አቭዬሽን አስተዳደር

የኢትዮጵያ ዓየር መንገድ ልዩ መቆጣጠሪያ የተደረገባቸውን አዲሶቹ ቦይንግ 737 Max 8 አውሮፕላኖች ሊከስቱ የሚችሉትን የተለየ ጠባይ ለመቋቋም “ያግዛል” የተባለ ልዩ መሳሪያ ከመለማመጃው ምስለ በረራ ላይ በመግጠም ሌሎች ዓየር መንገዶችን ቢቀድምም፤ በቅርቡ ቢሾፍቱ አቅራቢያ የተከሰከሰው የኢትዮጵያ ዓየር መንገድ የበረራ ቁጥር 302 አብራሪ ግን “በተለይ በዚህ አዲስ መሳሪያ ላይ ልምምድ አላደረጉም” ሲል የኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣ በትላንትናው ዕለት ዘገበ።

የኢትዮጵያ ዓየር መንገድ በበኩሉ በዛሬው ዕለት ይህንኑ አስመልክቶ ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ ቦይንግ የአውሮፕላኑ አብራሪዎች እንዲወስዱ የሚመክረውንና የዩናይትድ ስቴትሱ የአቭዬሽን ባለ ሥልጣን ማረጋገጫ የሰጠባቸውን አስፈላጊ ስልጠናዎች በሙሉ አብራሪዎቹ መውሰዳቸውን ጠቅሶ የኒውዮርክ ታይምሱን ዘገባ አጣጥሏል።

የዓየር መንገዱን መግለጫ፣ የቀደመውን የኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣና ሰሞንኛ ተያያዥ ዜናዎች እንመለከታለን።

ለተጨማሪ ዘገባ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የኢትዮጵያ ዓየር መንገድ አውሮፕላን አደጋ መንስዔ ፍለጋና ጥያቄዎቹ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:23 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG