በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የመን ጠረፍ ከተገለበጠው ጀልባ 25 አስከሬኖች ተገኙ


ፎቶ ፋይል፦ ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞች ራስ አል አራ፣የየመን ደቡባዊ ላሂጅ ክፍለ ሀገር የጠረፍ አካባቢ
ፎቶ ፋይል፦ ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞች ራስ አል አራ፣የየመን ደቡባዊ ላሂጅ ክፍለ ሀገር የጠረፍ አካባቢ

ሁለት መቶ የሚሆኑ ፍልሰተኞችን አሳፍሮ ሲጓዝ የመን ጠረፍ ላይ ከተገለበጠው ጀልባ ላይ ከነበሩት መካከል ሃያ አምስት አስከሬኖች መገኘታቸውን የየመን ባለሥልጣናት ተናገሩ።

ፍልሰተኞችን በድብቅ ማስተላለፊያ በሆነው እና የአካባቢው ነዋሪዎች "የገሃነመ እሳት በር" ብለው በሚጠሩት ራስ አል አራ የተባለው የየመን ደቡባዊ ላሂጅ ክፍለ ሀገር የጠረፍ አካባቢ አስከሬኖቹን ያገኙት አሳ አጥማጆች ማግኘታቸውን ነው ባለሥልጣናቱ ለአዣንስ ፍራንስ ፕሬስ የገለጹት።

ባለሥልጣኑ የመናዊያን ፍልሰተኞችን በድብቅ አስተላላፊዎችን ጠቅሰው በሰጡት ቃል ጀልባው ከሦስት ቀናት በፊት የተገለበጠው ቁጥራቸው ከአንድ መቶ ስድሳ እስከ ሁለት መቶ የሚደርስ ስደተኞችን ይዞ ሲጓዝ ነው፤ የተቀሩት ተሳፋሪዎች መጨረሻቸው ምን እንደሆነ ገና አልታወቀም ብለዋል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዓለም አቀፍ ፍልሰተኞች ድርጅት /አይኦኤም/ ጀልባው በአካባቢው መስጠሙን አረጋግጦ ስለአደጋው ያሉትን መረጃዎች በማጣራት ላይ መሆኑን አመልክቷል።

ጅቡቲን ከየመን ጋር በሚለየው እና ለህገ ወጥ አስተላላፊዎች ዋና የስደተኛ ማጥመጃ በሆነው የራስ አል አራ አካባቢ አስከሬናቸው የተገኙት ሰዎች፣ አፍሪካውያን ናቸው ብለው እንደሚያምኑ አሳ አጥማጆቹ ለኤኤፍፒ ገልጸዋል።

ባለፉት ቅርብ ወራትም ዋና የዓለም አቀፍ ንግድ መስመር እና የህገ ወጥ አዘዋዋሪዎች መናሃሪያ በሆነው በባኤል መንደብ ሰርጥ ላይ በርካታ ፍልሰተኞች ህይወታቸውን አጥተዋል።

XS
SM
MD
LG