በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በብሪታንያ የጭነት መኪና ኮንቴነር ውስጥ 39 አስከሬኖች ተገኙ


ብሪታንያ በአንድ የጭነት መኪና ኮንቴነር ውስጥ 39 አስከሬኖች ተገኝተዋል።

የብሪታንያ ፖሊስ በገለፀው መሰረት፣ የጭነት መኪናው ግረይስ ውስጥ በሚገኝ ዋተርግሌድ በተባለው ኢንዳስትሪያል ፓርክ ነው። ቦታው ከለንዶን 32 ኪሎሜትር ይርቃል። የ38 ጎልማሶችና የአንድ በአስራዎቹ የዕድሜ ክልል የነበረ ልጅ አስከሬኖች ናቸው የተገኙት።

የጭነት መኪናው ከቡልጋርያ ተነስቶ፣ ብሪታንያ የገባው ባለፈው ሳምንት ማብቆያ ላይ ነው የሚል ዕምነት አላቸው መርማሪዎች። የጭነት መኪናውን ነዳ የተባለ የ25 ዓመት ዕድሜ የሰሜን አየርላንድ ተወላጅ በግድያ ተጠርጥሮ ተይዟል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG