በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“ባብ ማርሊ፡ ዋን ላቭ” ፊልም አንደኝነቱን ይዟል


“ባብ ማርሊ፡ ዋን ላቭ”
“ባብ ማርሊ፡ ዋን ላቭ”

በሬጌ ስልት አቀንቃኙ ባብ ማርሊ ሕይወትና ሥራ ላይ ያተኮረውና ባለፈው ማክሰኞ የተለቀቀው “ባብ ማርሊ፡ ዋን ላቭ” ፊልም በአሜሪካ በሳምንቱ መጨረሻ 27.7 ሚሊዮን ዶላር የሲኒማ ገቢ በማግኘት አንደኝነቱን ይዟል። ፊልሙ የአንደኝነትን ሥፍራ ይይዛል ተብሎ እንዳልተጠበቀ ታውቋል።

በገጸ ባህሪ ጀግንነት ላይ ከተመሠረቱት ፊልሞች ተርታ የሚመደበው “ማዳም ዌብ” ቀዳሚውን ሥፍራ ይይዛል ተብሎ ቢጠበቅም፣ እስከ አሁን በተመሳሳይ ጭብጦች ላይ ተመሥረተው ከተሰሩ ፊልሞች ዝቅተኛውን ገቢ አግኝቷል ተብሏል።

ሁለቱም ፊልሞች ባለፈው ማክሰኞ የተለቀቁት፣ በማግስቱ በነበረው የፍቅር ቀን ሲኒማ ተመልካቾችን ለመሳብ ታልሞ የነበረ ቢሆንም “ዋን ላቭ” በቲያትር ቤቶች ተመራጭ ሆኗል።

የፊልሙ አዘጋጅ “ፓራማውንት ፒክቸርስ” ዛሬ የሚከበረውን የፕሬዝደንቶችን ቀን ጨምሮ 51 ሚሊዮን ዶላር እንደሚያገኝ ግምቱን አስቀምጧል። ከአሜሪካ ውጪ ካሉ 47 አገራት ደግሞ 29 ሚሊዮን ዶላር እንደሚያስገኝ ይጠበቃል።

በ70 ሚሊዮን ዶላር ወጪ የተሰራው “ዋን ላቭ”፣ ባብ ማርሊ በእ.አ.አ 1977 “ኤክሶደስ” ብሎ የሰየመውን አልበም ካዘጋጀበት፣ በአገሩ ጀማይካ ታላቅ የሙዚቃ ትዕይንት እስካቀረበት ያለውን ሂደት የሚያሳይ ሲሆን፣ የቤተሰብ ዓባላቱም በፊልም ዝግጅቱ መሳተፋቸው ታውቋል።

“ሰዎች ፊልሙን በመቀበላቸው እና የ’ዋን ላቭ’ መልዕክት ትኩረት እንዲያደርግ በመርዳታቸው እናመሰግናለን” ብሏል በፊልሙ ዝግጅት የተሳተፈውና የባብ ማርሊ ልጅ የሆነው ዚጊ ማርሊ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG