በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በደቡብ ሱዳን ናይል ወንዝ ውስጥ ጀልባ ሰጠመ


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

በደቡብ ሱዳን ወደሚገኘው ፋንጋክ ከፍለ ግዛት ያመራ የነበረ የምግብ ረድዔት የጫነ ጀልባ ባለፈው ዕሁድ ተገልብጦ መስመጡን አንድ የጀልባ ሰራተኞች ማኅበር ባለሥልጣን ለአሜሪካ ድምፅ ራድዮ ተናግረዋል።

ጀልባው ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዓለም ምግብ ፕሮግራም የተላከ ረድዔት ጭኖ በጃንግሌይ ክፍለ ግዛት ከሚገኛው ቦር ወደ ፋንጋክ ክፍለ ግዛት ሲጓዝ በናይል ወንዝ ተገልብጦ እንደሰመጠ ቦር ያለው የጃንግለይ የጀልባ ሰራተኞች ዋና ጸኃፊ ኤሊጃህ ቶንግቦር ጠቁመዋል። ጉዳት ደርሶ እንደሆነ አልተገለጸም።

ጀልባው መጫን የሚገባው 80 ሜትሪክ ቶን ብቻ ሆኖ ሳለ የጫነው ግን 90 ሜትሪክ ቶን ረድዔት እንደነበር ታውቋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG