በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"ሰማያዊ እና ግራጫ - ይህ የስደት ዘመን" አውደ ርዕይ


ሰዓሊ እና ገጣሚ ከበደች ተክለአብ
ሰዓሊ እና ገጣሚ ከበደች ተክለአብ

በቅርቡ ዋሽንግተን ላይ ለእይታ የበቃ አውደ ርዕይ ነው። እውቋ ባለ ብዙ ዘርፍ የሥነ ጥበብ ባለሞያ፡ ሰዓሊ፣ ቀራጺ፣ ገጣሚ እና መምህርት ከበደች ተክለአብ ከሌላ ታዋቂ አሜሪካዊ ባለ ቅኔ ጋር በትብብር ያሳየችው ነው።

በተለይ በስደት እና ከቀያቸው ተነጥለው ለፍልሰት የተዳረጉ አያሌዎች ከመንገዳቸው የሚገጥማቸውን መከራ እና እንግልት፤ ከሚኖሩበት መንደር በአካል ባይርቁም ባሉበት የተዘነጉትን እጣና የሕይወት ምስቅልቅል ጭምር የሚቃኙ ጥበባዊ ሥራዎች ናቸው።

"ሰማያዊ እና ግራጫ - ይህ የስደት ዘመን" አውደ ርዕይ
please wait

No media source currently available

0:00 0:14:38 0:00

በዋሽንግተኑ የአሜሪካን ዩኒቨርሲቲ ቤተ-መዘክር እንደ አውሮፓውያኑ የቀን አቆጣጠር ከሰኔ 17/2023 እስከ ነሃሴ 13/2023 ሁለት ወራት ለተቃረበ ጊዜ በታየው አውደ ርዕይ ለእይታ የቀረቡ ሥራዎችን እና የዝግጅቱን መነሻዎች ጨምሮ የሚያስቃኘውን ሰዓሊ ከበደች ተክለአብ ከአሜሪካ ድምጽ ጋር ያደረገችውን ቆይታ ከተያያዘው የድምጽ ማጫወቻ ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG