በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ብሊንከን ከኢራቁ የኩርድ ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር ዋሽንግተን ውስጥ ይነጋገራሉ


የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን የኢራቁ የኩርዲስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ማስሩር ባርዛኒን ዛሬ ሰኞ እዚህ ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ በሚገኘው ዋና ጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው ያነጋግራሉ፡፡

ብሊንክን በደቡብ አሜሪካ አርጀቲና ያደረጉትን የሶስት ቀናት ጉብኝት ያጠናቀቁት ባለፈው ዓርብ ነበር፡፡

በአርጀኒቲናው ቆይታቸው ቦነስ አይረስ ከሚገኘው በካሳ ሮዳ የፕሬዚዳንቱ ቤተመንግሥት ውስጥ አዲስ በተሰየሙት ፕሬዚዳንት ጃቬል ሚሌ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡

ብሊንከን ከአርጀንቲናው አቻቸው ዲያ ሞንዲኖ ጋር ተገናኝተው መወያየታቸውም ተመልክቷል፡፡

የብሊንከን ጉዞ የተጀመረው ብራዚል ውስጥ በተካፈሉበት የቡድን 20 ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ሲሆን፣ በቆይታቸውም ከብራዚሉ ፕሬዚዳንት ሉዊ ኢናሲዮ ሉላ ደ ሲልቫ ጋር በሁለትዮሽና ዓለማአቀፍ ጉዳዮች ላይ ከተነጋገሩ በኋላ ነው፡፡

ብሊንክን ዛሬ ሰኞ ከፖላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ራዶስላው ሲኮርስኪ ጋር ተገናኝተው እንደሚወያዩ ተነግሯል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG