በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አገራት ለዩክሬን የሚያደርጉትን ድጋፍ ቀጥለዋል


ዩክሬን ፕሬዝደንት ቮሎዲሚር ዜሌንስኪ
ዩክሬን ፕሬዝደንት ቮሎዲሚር ዜሌንስኪ

ሩሲያ ካደረሰችባት ወረራ ዩክሬንን መታደግ እና እንድታገግም ማድረግ ለዓለም አንድነት፣ መረጋጋት እና ዲሞክራሲ እንዲሁም ሥራ ፈጠራ አስተዋጽኦ እንደማድረግ ይቆጠራል ሲሉ የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ቮሎዲሚር ዜሌንስኪ ትናንት አገሪቱን ለመርዳት በለንደን በተካሄደ ጉባኤ ላይ ተናገሩ።

ስድሳ አገራት እና የግሉ ዘርፍ፣ እንግሊዝ እና ዩክሬክ በጋራ ለንደን ላይ ባዘጋጁት የሁለት ቀን ጉቤኤ ላይ ተሳትፈዋል።

የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክ ለሆስፒታል እና ትምህርት ቤት መልሶ ግንባታ የሚውል 3 ቢሊዮን ዶላር የዓለም ባንክ ብድር ማስተማመኛ ለዩርክሬን እንደሚሰጡ ቃል ገብተዋል።

የአሜሪካው የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን በበኩላቸው አገራቸው ተጨማሪ 1.3 ቢሊዮን ዶላር እንደምትሰጥ አስታውቀዋል። ገንዘቡ የዩክሬንን የኃይል መዋቅር ለማደስ፣ ድንበሯን ለማዘመን፣ በቡር እና ወደቦችን እናዲሁም የጉምሩክ አሰራርን ለማሳለጥ እና የንግዱ ማሕበረሰብን ለማገዝ እንደሚውል ብሊንከን ገልጸዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ አገራቸው ከ30 በላይ ሻሂድ ድሮኖችን ሰኞ ምሽት መትታ መጣሏን ዜሌንስኪ ትናንት በምሽት የቪድዮ መልዕክታቸው አስታውቀዋል። አንድ የአደጋ ግዜ ሠራተኛ መገደሉን እና 8 ሌሎች ደግሞ መጎዳታቸውንም ጠቁመዋል።

XS
SM
MD
LG