በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ብሊንከን በአውስትራሊያው ጉባኤ


የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን በሜልበርን አውስትራሊያ አውሮፕላን ጣቢያ ሲደርሱ ሚካኤል ጎልድማን እንኳን ደህና መጡ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን በሜልበርን አውስትራሊያ አውሮፕላን ጣቢያ ሲደርሱ ሚካኤል ጎልድማን እንኳን ደህና መጡ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የዩናይትድ ስቴትሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን በአውስትራሊያ ጉዟቸው በእስያ-ፓሲፊክ እና በኢንዶ-ፓሲፊክ ክልሎች አራቱን አገሮች ዩናይትድ ስቴትስን፣ አውስትራሊያን፣ ጃፓንን እና ህንድን ካካተተው ቡድናቸው ጋር የሚያደርጓቸው ምክክሮች "በክልሉ እና በዓለም ዙሪያ ላሉ ህዝቦች" የሚበጁ ያሏቸው እና የባይደንን አስተዳደር ይበልጥ ትኩረት የሚያደርግባቸው ጉዳዮች መሆናቸውን አመላከቱ።

ብሊንከን "ኳድ" በሚል መጠሪያ ለሚታወቀው የአራቱ አገሮች ቡድን ስብሰባ በመዘጋጀት ላይ ባሉበት ወቅት ነው አብረዋቸው ለተጓዙት ጋዜጠኞች ከሃገራቱ ጋር ተባብረው ስለሚሰሯቸው ጉዳዮች የተናገሩት። "ኳድ" የኮሮናቫይረስ ክትባቶችን በዓለም ዙሪያ ለማድረስ ሁነኛ መንገድ ሆኖ እያገለገለ መሆኑን፡ የተናገሩት ብሊንከን፤ “የባህር ደህንነትን በማጠናከር እና በኢንዶ-ፓሲፊክ ክልል ውስጥ የሚታየውን የኃይል ጥቃት እና እንዲሁም በማስገደድ የሚፈጸሙ ድርጊቶች ለመቋቋም እየሰራ ነው” ብለዋል።

አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች በአዎንታዊ መንገዶች ጥቅም የሚውሉበትን መንገድ ለማረጋገጥ በጋራ መሥራት፤ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣ ሰፊ እና ጥልቅ አጀንዳ መሆኑንም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

XS
SM
MD
LG