በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ብሊንከን ስለዩክሬይን ስለኔቶና ስለደኅንነት ጉዳዮች አውሮፓ ናቸው


ዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን
ዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን

ዩክሬን የሩሲያን ወረራ ለመመከት ለምታካሂደው ጦርነት ድጋፍና እርዳታ ለመስጠት የኔቶ አባል አገሮች “ያላቸውን ቁርጠኛነት ለማደስ እያደረጉ ያሉትን እንቅስቃሴ ዩናይትድ ስቴትስ ትቀላቀላለች” ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን አስታወቁ።

ብሊንከን ዛሬ በተጀመረው የሰሜን አትላንቲክ የጦር ትብብር ድርጅት (ኔቶ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ ለመገኘት ብራስልስ ናቸው።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከነገ በስተያ (ረቡዕ) የዩናይትድ ስቴትስ ልዑካንን መርተው የአውሮፓ የደኅንነትና የትብብር ድርጅት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮችን ስብሰባ ወደምታስተናግደው ሰሜን መቄዶንያ እንደሚዘልቁ ተዘግቧል።

ዩናይትድ ስቴትስ 75ኛ ዓመቱን የፊታችን መጋቢት 26 የሚደፍነውን የኔቶን መጭ ጉባዔ የፊታችን ሃምሌ ዋሺንግተን ዲ.ሲ. ላይ ታስተናግዳለች።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG