በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ብሊንክን ወደ ምዕራብ አፍሪካ አቀኑ


የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን

ለስድስት ቀናት የሚቆየውን የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት ጉብኝት ዛሬ የጀመሩት የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን፣ ኬፕ ቨርዴ ገብተዋል። በቆይታቸውም ከአፍሪካ መሪዎች ጋራ በቀጠናዊ የፀጥታ ችግሮች ዙሪያ ይወያያሉ ተብሏል።

አራት የአፍሪካ ሀገራትን ለመጎብኘት ትላንት ከዋሽንግተን ዲሲ የተነሱት አንተኒ ብሊንከን፤ጉብኝታቸውን ከኬፕ ቨርዴ ጀምረዋል። ቀጣይ ጉዟቸውን ወደ አይቨሪ ኮስት፣ ናይጄሪያና አንጎላ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በአፍሪካ የሁለትዮሽ ንግድን ለማሳደግ፣ በአገር ውስጥ እና በአህጉሪቱ የሥራ እድል ለመፍጠር፣ እንዲሁም አፍሪካ በዓለም አቀፍ ገበያ እንድትወዳደር የሚያግዝ መንገድ”

የብሊንከን የጉዞ መርሃ ግብር የወደብ ከተማዋን ለማዘመን ከዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ሚሊኒየም ቻሌንጅ ኮርፖሬሽን የገንዘብ ድጋፍ ያገኘችው የፖርቶ ዳ ፕራያ ወደብ ከተማን መጎብኘትን ያካተተ ነው።

በአይቮሪ ኮስትና ኢኳቶሪያል ጊኒ መካከል የሚካሄደውን የአፍሪካ ዋንጫ የእግር ኳስ ውድድር እንደሚከታተሉ እቅድ ተይዟል።

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ቃል አቀባይ ማቲው ሚለር ከጉዞው በፊት እንደተናገሩት ብሊንከን ዩናይትድ ሴትትስ በአፍሪካ የሚኖራት የመሰረተ ልማት ኢንቨስትመንት፣ “በአፍሪካ የሁለትዮሽ ንግድን ለማሳደግ፣ በአገር ውስጥ እና በአህጉሪቱ የሥራ እድል ለመፍጠር፣ እንዲሁም አፍሪካ በዓለም አቀፍ ገበያ እንድትወዳደር የሚያግዝ መንገድ” መሆኑን አፅንዖት ይሰጣሉ ተብሏል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG