በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ብሊንከን ሊገላግሉ እሥራኤል ናቸው


የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን ዛሬ ቴል አቪቭ ገብተዋል
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን ዛሬ ቴል አቪቭ ገብተዋል

በፍልስጥዔምና በእሥራኤል መካከል በቅርቡ ተቀስቅሶ የተካረረው ግጭት በአስቸኳይ እንዲቆምና ውጥረቱ እንዲረገብ ለማስቻል በሚቻልበት መንገድ ላይ ለመምከር የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን ዛሬ ቴል አቪቭ ገብተዋል።

ግብፅ ውስጥ ካደረጉት አጭር ቆይታ በኋላ እሥራኤል የገቡት ብሊንከን ፍልስጥዔማዊያኑ በእሥራኤላዊያን ላይ አድርሰዋቸዋል ያሏቸውን በቅርብ የተፈፀሙ ጥቃቶች አውግዘዋል።

ይሁን እንጂ በማንም ሲቪል ላይ የሚደርስ ጉዳት ተቀባይነት እንደሌለው የተናገሩት አሜሪካዊው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እሥራኤል ከአፀፋ እምርጃ እንድትታቀብ አሳስበዋል።

“በሽብር አድራጎት የንፁሃንን ህይወት መቅጠፍ ምንጊዜም ቢሆን አረመኔያዊ ወንጀል ነው - ያሉት ብሊንከን ባለፈው ዓርብ ከአንድ ኢየሩሳሌም ከሚገኝ ምኩራብ ሲወጡ የተገደሉት ሰባት ሰዎችን በማስታወስ “በተለይ ሰዎችን በአምልኮ ሥፍራቸው ደጃፍ ላይ ዒላማ ማድረግ እጅግ በጣም አስደንጋጭ ነው” ብለዋል።

የሰሞኑ አመፅ የተቀሰቀሰው በሰባት እሥራኤላዊያን ላይ የተፈፀመን ግድያ ለመበቀል በሚል የእስራኤል ወታደሮች የታጣቂዎቹ ጠንካራ ይዞታ የሆነውን የዌስት ባንኳን ጀኒንን ወርረው የበዙት ታጣቂ የሆኑ አሥር ሰዎችን ከገደሉ በኋላ መሆኑ ተነግሯል።

ብሊንክን ከእሥራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤጃንሚን ኔታኒያሁና ከፍልስጥዔሙ ፕሬዚዳንት መሃሙድ አባስም ጋር ተገናኝተው እንደሚነጋገሩ ቀደም ሲል ተገልጿል።

XS
SM
MD
LG