የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን በዛሬው ዕለት ቴል አቪቭ ላይ ከእስራኤል መሪዎች ጋር ተገናኝተው የጋዛው ጦርነት ወደ ሌሎች አካባቢዎች እንዳይዛመት ለመከላከል፣ የእስራኤል ባለሥልጣናት የሲቪሎችን ደህንነት እንዲጠበቅ ይበልጥ እንዲተጉ እና እንዲሁም የሰብአዊ ረድኤት ወደ ጋዛ የሚደርስበትን መንገድ በማመቻቸት ላይ ያተኮሩ ውይይቶችን ይዘዋል።
ብሊንከን ከእስራኤሉ ፕሬዚዳንት አይዛክ ሄርዞግ ጋር ሆነው በሰጡት አስተያየት ከተወሰኑት ታጋቾች ቤተሰብ አባላት ጋር እንደሚገናኙ ተናግረዋል።
“ወደ በርካታ የቀጠናው ሀገራት፣ ቱርክ፣ ግሪክ፣ ዮርዳኖስ፣ ኳታር፣ የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ እና ሳዑዲ አረቢያ ካደረግኩት ጉዞ መመለሴ ነው” ያሉት ብሊንከን ከእነኚህ ሃገራት መሪዎች ከሰማሁትን ጥቂቱን ለፕሬዚዳንቱ፣ ለጠቅላይ ሚኒስትሩና ለካቢኔያቸው አባላት ማካፈል እፈልጋለሁ’ ብለዋል።
ወደ በርካታ የቀጠናው ሀገራት፣ ቱርክ፣ ግሪክ፣ ዮርዳኖስ፣ ኳታር፣ የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ እና ሳዑዲ አረቢያ ካደረግኩት ጉዞ መመለሴ ነው”
አያይዘውም ከአንዳንድ የታጋቾች ቤተሰቦች ጋር ለመገናኘት እና የታገቱት በሙሉ ተለቀው ወደ ቤታቸው ይመለሱ እና ከቤተሰቦቻቸው ጋር ይቀላቀሉ ዘንድ እያደርግን ስላለነው ያላሰለሰ ጥረት ለመወያየት እድል ይኖረናል። ቀጣዩን አቅጣጫ ጨምሮም ብዙ ልንነጋገርባቸው የምንችላቸው ነገሮች አሉ።” ብለዋል።
በትላንትናው ዕለት ከብሊንከን ጋር ተገናኝተው የተነጋገሩት የሳዑዲው አልጋ ወራሽ መሀመድ ቢን ሳልማን በበኩላቸው በሰጡት አስተያየት፡ በጋዛ ሰርጥ ያለውን ወታደራዊ እንቅስቃሴ ማቆም አስፈላጊ ስለመሆኑ፣ እንዲሁም ሰላም እና መረጋጋት ማምጣት የሚያስችል ሁኔታ የመፍጠርን አስፈላጊነት አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።
በሃማስ ታጣቂዎች እና በእስራኤል ኃይሎች መካከል የተፈጠረውን ግጭት ተከትሎ ሳዑዲ አረቢያ ከእስራኤል ጋር ያላትን ግንኙነት ወደ መደበኛ ሁኔታ ለመመለስ በሚያስችል መንገድ ዙሪያ የጀመረችውን ዲፕሎማሲያዊ ንግግር ማቋረጧ ይታወሳል።
ዩናይትድ ስቴትስ በበኩሏ እስራኤል በጋዛ የያዘችውን ጦርነት ወደ አነስተኛ ወታደራዊ ዘመቻ ታሸጋግር ዘንድ አሳስባለች። ሆኖም የአረብ አገሮችን የያዙትን የተኩስ አቁም ጥያቄ ቸል ብላ እስራኤልን መደገፏን ቀጥላለች።
መድረክ / ፎረም