በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“በጋዛ በየቀኑ ሕይወታቸውን የሚያጡት ሲቪሎች ቁጥር እጅግ ከፍተኛ ነው” - ብሊንከን


የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሯ አንተኒ ብሊንከን
የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሯ አንተኒ ብሊንከን

በጋዛ በየቀኑ ሕይወታቸውን የሚያጡት ሲቪሎች ቁጥር እጅግ ከፍተኛ መሆኑን ዩናይትድ ስቴትስ ታምናለች ሲሉ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሯ አንተኒ ብሊንከን ትናንት ቴል አቪቭ ላይ ተናግረዋል።

ሆኖም ግን፣ እስራኤል የዘር ማጥፋት በመፈፀም ላይ ነች በሚል በደቡብ አፍሪካ የሚቀርበው ክስ ተገቢ እንዳልሆነ ብሊንከን አስታውቀዋል።

ብሊንከን አስተያየታቸውን የሰጡት ከእስራኤል ባለሥልጣናት ጋር ከተነጋገሩ በኋላ ቴል አቪቭ ላይ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ነው።

ፍልስጤማውያን ሁኔታው ሲፈቅድ ወደ መኖሪያቸው መመለስ እንዳለባቸው የተናገሩት ብሊንከን፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጋዛ ውስጥ ያለውን ሁኔታ እንዲገመግም ዕቅድ እንዳለም አመልክተዋል።

“ጠላት በሲቪሎች መሃል፣ በትምህርት ቤቶች እና በሆስፒታሎች በሚደበቅበት ሁኔታ ውስጥ የሲቪሎችን ሕይወት ከአደጋ መጠበቅ አስቸጋሪ ቢሆንም፣ በጋዛ በተለይም በሕፃናት ላይ የደረሰው ሞት እጅግ ከፍተኛ ነው” ሲሉ ተደምጠዋል ብሊንከን።

“እስራኤል በዓለም አቀፍ የወንጀል ችሎት የዘር ማጥፋት ፈጽማለች የሚል ክስ መቅረቡ፣ ዓለም ግጭቱን ለማስቆም የሚያደርገውን ጥረት ያደናቅፋል” ያሉት ብሊንከን “ሐማስ፣ ሄዝቦላ፣ ሁቲ እና በኢራን የሚገኙ ደጋፊዎቻቸው እስራኤልን ለማጥፋት እና በይሁዶች ላይ ጭፍጨፋ እንዲካሄድ ጥሪ ማድረጋቸውን ስናይ ክሱን ስላቅ ያደርገዋል” ሲሉ አክለዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG