በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ብሊንከን ወደ አይስላንድ ተጓዙ


የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን በአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ እና በአርክቲክ ካውንሲል የሚኒስትሮች ስብሰባ ለመካፈል ወደአይስላንድ ዋና ከተማ ሬኬቪክ ተጉዘዋል።

ዛሬ ማክሰኞ ብሊንከን ከአይስላንድ ፕሬዚደንት ጉድኒ ዮሃንሰን እና ከጠቅላይ ሚኒስትር ካትሪን ጃኮብስዶቲር ጋር የሚነጋገሩ ሲሆን ውይይታቸው የአየር ንብረት ለውጥ፣ ሰብዓዊ መብቶች፣ የሁለቱን ሃገሮች የሁለትዮሽ ግንኙነት እና አርክቲክን በመሳሰሉ ቅድሚያ ትኩረቶች የሀገሮቻቸውን ትብብር ላይ እንደሚያተኩሩ ክዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቲር የወጣው መግለጫ አመልክቷል።

ነገ በሚካሄደው የአርክቲክ ካውንሲል የሚኒስትሮች ጉባኤ ጎን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ብሊንከን ለመጀመሪያ ጊዜ ከሩስያው አቻቸው ሴርጌይ ላቭሮቭ ጋር ይገናኛሉ፤ ሁለቱ ሚኒስትሮች የሚገናኙት የዩናይትድ ስቴትስ እና የሩስያ ውጥረት በተባባሰበት በዚህ ወቅት ሲሆን በተጨማሪም ለሚቀጥለው ወር የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን እና የሩስያ ፕሬዚደንት ቪላዲሚር ፑቲን ጉባኤ ዝግጅቶችን የሚያመቻች እንደሚሆን ተገልጿል።

XS
SM
MD
LG