በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቡድን 7 አባል አገራት ቻይና ሩሲያ ማይነማርና ሶሪያን ተነጋገሩ


የቡድን ሰባት አባል አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ በለንደን
የቡድን ሰባት አባል አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ በለንደን

የቡድን ሰባቱ የበለጸጉ አገሮች የውጭ ጉዳይ ምኒስትሮች ዛሬ ማክሰኞ ለንደን ላይ ተሰብስበዋል፡፡ በቻይና እና በሩሲያ፣ በማይናማሩ መንፈንቀለ መንግስት፣ በሶሪያው ግጭትና በአፍጋኒስታን ስላለው ወቅታዊ ሁኔታን ጨምሮ በተለያዩ ዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ላይ እንደሚነጋገሩ ይጠበቃል፡፡

“ስብሰባውን የሚመሩት የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶሚንክ ራብ ሲሆኑ፣ ስብሰባው የዴሞክራሲን የነጻትና ሰብአዊ መብት ጉዳዮችን አደጋ ላይ ሊጥሉ በሚችሉ አካባቢያዊ የፖለቲካ ጉዳዮች ላይ ይነጋገራል” ሲል የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ራብ ከዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን ጋር አስቀድመው ትናንት ሰኞ የተነጋገሩ ሲሆን፣ የቡድን 7 አባል አገሮች፣ ለማይናማር ህዝብ የሰአብአዊ እርዳታ በሚጨመርበትና፣ የጦር መሳሪያ ማዕቀብ በሚደረግበት፣ እንዲሁም ከማያናማር ወታደራዊ ጁንታ ጋር ግንኙነት ባላቸው ግለሰቦችና ተቋማት ላይ ማዕቀብ ስለሚጣልበት ሁኔታ ግፊት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ይህን አስመልከቶ የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶምኒክ ራብ እንዲህ ብለዋል

“በማይናማር ጥቃቱ እንዲያበቃ እንፈልጋለን፡፡ ወታደራዊ አገዛዙ ወደ ተመረጠ ዲሞክራሲያዊ አስተዳደር እንዲመለስና ሥልጣን በህዝብ ወደ ተመረጡ ተወካዮች እንዲመለስ እንሻለን፡፡ እኛ ኢላማ በምናደጋቸው እዚህ በምንጥለው ማዕቀብ ብቻ አንወሰንም፡፡ የእንግሊዝ የንግድ ድርጅቶች የማይናማር ሠራዊት ከሚቆጣጠሯቸው የንግድ ድርጅቶች ጋር ሁሉ የሚያደርጓቸውን ግንኙነቶች በሙሉ እንዲያቋርጡ እርምጃ የሚወሰድበትን መንገድ ነው የምንመለከተው፡፡ በዚያም በኩል ግፊት ለማድረግ እንሞክራለን፡፡”

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ብሊነክን፣ “ዩናይትድ ስቴትስ ከሰሜን ኮሪያ ጋርየዲፕሎማሲ ግንኙነት በማድረግ፣ የኮሪያን ባህረሰላጤን ከኒዩክለር ነጻ የማድረግ ግቧን ለማሳከት፣ ሰሜን ኮሪያን አስመልክቶ ለረጅም ወራት የነበራትን ፖሊሲ እንደገና ትቃኛለች፡፡” ብለዋል፡፡

የቡድን 7 አባል አገራት ቻይና ሩሲያ ማይነማርና ሶሪያን ተነጋገሩ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:06 0:00

አሜሪካ በሰሜን ኮሪያ ያለውን የሰአብዊ መብት ጉዳዮች የሚከታተል ልዩ ልኡክ እንደምታቋቁምም ብሊንከን ተናግረዋል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አንተኒ ብሊንከን እንዲህ ብለዋል

“አሁን ያለን ፖሊሲ በሚገባ የተቃኘ፣ ከሰሜን ኮሪያ ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለማድረግ ክፍት የሆነና የዩናይትድ ስቴትስን፣ የአጋሮቻችንና በአካባቢው ያሰማራናቸውን ኃይሎቻችንን ደህንነት በጠበቀ መልኩ ተግባራዊ ሊደረግ የሚችል አቀራረብ ነው፡፡

እሱን እያደረግንም ከአጋሮቻችንና ወዳጆቻችን፣ የደቡብ ኮሪያ ሪፐብሊክን ጨምሮ፣ ከጃፓናን በሂደት ከሚመጡ ሌሎች አገሮችም ጋር በቅንጅትና በመመካከር እንሰራለን፡፡”

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቹ ስበሰባ የተካሄደው በመጭው ሰኔ እዚያው እንግሊዝ ውስጥ ይደረጋል ለተለባለው የቡድን 7 አባል አገራት መሪዎች መሆኑም ሁኔታዎችን ለማመቻቸት መሆኑም ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG