በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሩሲያ ወረራ ዓምባገነንነት በዴሞክራሲ ላይ የጋረጠው አደጋ ማሳያ ነው - ብሊንከን


 “ለሰላም ሲባል ብቻ የሰላም ሥምምነት አይደረግም” - የዩክሬን የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:32 0:00

“ለሰላም ሲባል ብቻ የሰላም ሥምምነት አይደረግም” - የዩክሬን የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር

“ለሰላም ሲባል ብቻ የሰላም ሥምምነት አይደረግም” - የዩክሬን የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ኹለተኛውን ዓለም አቀፍ የዴሞክራሲ ጉባኤ በማካሔድ ላይ ይገኛል፡፡ 120 የሚኾኑ ሀገራት ተወካዮች እንዲሁም፣ የሲቪል ማኅበራት እና የቴክኖሎጂ ኩባንያ ተወካዮች፣ በጉባኤው ላይ በመሳተፍ ላይ ናቸው፡፡ የሚበዙት ተሳታፊዎች በርቀት(በኢንተርኔት) በሚከታተሉት ጉባኤ ላይ፣ ዴሞክራሲያዊ ባልኾነ ፖሊሲያቸው የሚወቀሱት እንደ ሕንድ፣ እስራኤል እና ፖላንድ የመሳሰሉ ሀገራት በመሳተፍ ላይ ናቸው፡፡ የጉባኤው የትላንት ማክሰኞ ውሎ ያተኮረው፣ በዩክሬን ላይ ነበር፡፡

የዩክሬኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲሚትሮ ኩሌባ፣ በአሜሪካ በተዘጋጀው የዴሞክራሲ ጉባኤ ላይ፣ በቪዲዮ በአደረጉት ንግግር፣ “የዩክሬን ሕዝብ ከማንም በላይ ሰላምን ይሻል፤ ነገር ግን ለሰላም ሲባል ብቻ የሰላም ስምምነት አይደረግም፤” ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

“የዩክሬን ሕዝብ የሰላምን ጥሪ የሚቀበለው፣ ሙሉ በሙሉ የሩሲያን ጠብ አጫሪነት የሚያስቆም፣ የሩሲያ ጦር ሙሉ ለሙሉ ከዩክሬን ግዛት የሚወጣ ከኾነና የአገራችን ድንበር ዓለም ወደሚያውቀው ሉዓላዊ የድንበር ክልል የሚመለስ ከኾነ ነው፤” ሲሉ አጽንዖት ሰጥተው ተናግረዋል - ኩሌባ፡፡

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን፣ ትላንት በጉባኤው ላይ በአደረጉት ንግግር፣ “ሩሲያ በዩክሬን ላይ የፈጸመችውን ወረራ ያህል፣ ፈላጭ ቆራጭነት በዴሞክራሲ ላይ የጋረጠውን አደጋ ግልጽ አድርጎ የሚያሳይ ምሳሌ የለም፤” ብለዋል፡፡

ብሊንከን ዩክሬንን በተመለከተ የቀረበውን የሰላም ሃሳብ ተቀብለው፣ በቻይና እና በሌሎችም የቀረበውን ሃሳብ የአገራቱን ስም ሳያነሱ ውድቅ አድርገዋል፡፡

“በቅን ልቡና የምናደርገውን ጥረት፣ ለምሳሌ፥ የተኩስ ማቆም ጥሪን በተመለከተ የምናደርገው ጥሪ፣ ምን ማለት እንደኾነ መገንዘብና ጥንቃቄ ማድረግ አለብን፡፡ ጊዜው፣ ሩሲያ በእጇ ያሉትን ድሎች የምታጠናክርበት ወይም ዕረፍት የምታደርግበትና እንደገና ተዘጋጅታ የምታጠቃበት ጊዜ አድርጋ ልትጠቀምበት ትችላለች፤” ሲሉ አክለዋል - ብሊንከን፡፡

በካቶሊክ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ ምሁር የኾኑት ማይክል ኪሜጅ፣ ለቪኦኤ እንደተናገሩት፣ “እየተካሔደ ባለው ኹለተኛው የዴሞክራሲ ጉባኤ ላይ፣ ፕሬዚዳንት ባይደን፣ በርካታ ፈተናዎች ገጥመዋቸዋል፡፡ የአሜሪካ የቅርብ ሸሪክ ከኾነችው እስራኤል ጋራ የተፈጠረው ውጥረት አንዱ ነው፤” ብለዋል፡፡

ነገር ግን አሉ የታሪክ ምሁሩ፣ “ለዩክሬን ድጋፍ ማግኘት የጉባኤው ዋና ትኩረት ነው፡፡”

“በእስራኤል እየታየ ያለው ክሥተት፣ አገሪቱ ዴሞክራሲን በተመለከተ የት ላይ እንዳለች የሚያሳይ ነው፡፡ በርካታ የአውሮፓ ሀገራት ወደነበሩበት ኹኔታ ተመልሰዋል፡፡ እንደሚመስለኝ፣ ለፕሬዚዳንት ባይደን ችግር የሚኾነው፣ እንደ ደቡብ አፍሪካ፣ ብራዚልንና ሕንድን የመሰሉ ዴሞክራሲያዊ ሀገራት፣ አሜሪካ የዩክሬኑን ጦርነት በተመለከተ ያላትን አቋም አለመደገፋቸው ነው፤” ሲሉ ኪሜጅ ከቪኦኤ ጋራ በአደረጉት ቃለ ምልልስ ተናግረዋል፡፡

ማይክል ኪሜጅ ለቪኦኤ እንዳሉት፣ በዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎዲሚር ዜሌኒስኪ መሪነት፣ ከፍተኛ የጦር ኃይል ባላት ሩሲያ ላይ፣ ዩክሬን እያስመዘገበች ያለችው ድል፥ አነቃቂ እና ዴሞክራሲን በዓለም ለማስፈን ለሚደረገው ጥረት የሚያነሣሣ ነው፡፡

XS
SM
MD
LG