በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስና ኮሎምቢያ የአደንዛዥ ዕፆችን ዝውውር ለማስቆም መከሩ


የዩናይትድ ስቴትስ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከንና የኮሎምቢያው ፕሬዚዳንት ጉስታቮ ፔትሮ
የዩናይትድ ስቴትስ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከንና የኮሎምቢያው ፕሬዚዳንት ጉስታቮ ፔትሮ

የአሜሪካው የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከንና የኮሎምቢያው ፕሬዚዳንት ጉስታቮ ፔትሮ የናርኮቲክ አደንዛዥ ዕፆች የባህር ላይ ዝውውርን ለመግታት የሚደረገውን ጥረት ከፍ ለማድረግና፣ በዕጽ ዝውውር ላይ የሚደረገውን የመረጃ ልውውጥም በተሻለ ደረጃ ለማካሄድ በሚያስችሉ መንገዶች ዙሪያ ለመነጋገር ትናንት ሰኞ መገናኘታቸውን አስታውቀዋል።

የቀድሞ ግራ ዘመም አማፂ የነበሩት ፔትሮ፣ አሜሪካ በህገ ወጥ አደንዛዥ እጾች ላይ የከፈተችውን ጦርነት አናንቀው፣ ችግሩን ለመፍታት አዲስ ዓለም አቀፋዊ አቀራረብ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

ብሊንከን በሰጡት መግለጫ፣ ሁለቱ ወገኖች በጀልባዎች በባህር ላይ የሚደረገውን የእጽ ዝውውር ለመግታትና፣ መረጃዎችን በመቀያየር ረገድ ብዙ ለመስራት አስበዋል ብለዋል።

በገጠር የሚኖሩ ሲቪሎችን ደህንነት ማሻሻልን በተመለከተ ከኮሎምቢያ ጋር እንደሚሰሩ ብሊንከን ተናግረው፣ ህግ አስከባሪዎች ላይ በማተኮር ብቻ ችግሩ እንደማይቀረፍ አመልክተዋል።

ፀጥታ መጓደል፣ ሙስና፣ በህግ አለመጠየቅ እና የፍትህ ዕጦት የስር መሰረት ምክንያቶችን መለየትና መፍትሄ መሻት እንደሚገባም ጠቁመዋል።

የአሜሪካው የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን ግራ ዘመም መሪዎች ባሏቸው ኮሎምቢያ፣ ቺሊ፣ እና ፔሩ አንድ ሳምንት የሚዘልቅ ጉብኝት በማድረግ ላይ ናቸው።

XS
SM
MD
LG