በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር የቱርክ ጉብኝት


የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን፣ የቱርክ ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን፣ በአንካራ፤ ቱርክ
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን፣ የቱርክ ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን፣ በአንካራ፤ ቱርክ

የባይደን አስተዳደር ዩናይትድ ስቴትስ ለቱርክ ኤፍ 16 ተዋጊ ጄቶች እንድትሸጥላት የሚደግፍ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንተኒ ብሊክን ተናገሩ፡፡ ብሊንክን ይህን የተናገሩት ከቱርክ መሪዎች ጋር ለመነጋገር ዛሬ በአንካራ ባደረጉት ጉብኝት ላይ ነው፡፡ ስዊድን እና ፊንላንድ በቅርብ ጊዜ የሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) አባል እንደሚሆኑ እንደሚተማመኑም ብሊንክን አስታውቀዋል፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ 40 ተዋጊ ጀቶችን እና ያረጁት ጀቶቿን ለማደስ የሚያስፈልጉ 80 ማዘመኛዎች እንድትሸጥላት ጠይቃለች፡፡

ይህን 20 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ሽያጭ ለማከናወን የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት ፈቃድ መስጠት አለበት፡፡ አንተኒ ብሊንከን ከቱርኩ አቻቸው መቭሉት ካቫስጉሉ ጋር ሆነው ባደረጉት ጋዜጣዊ ጉባዔ የጀቶች ሽያጩን ዕቅድ በዚህ ቀን ለምክር ቤት እናቀርባለን ብለው ቁርጥ ያለ የጊዜ ሰሌዳ ለመስጠት እንደማይችሉ ተናግረው ሆኖም የባይደን አስተዳደር የተዋጊ ጀቶች ሽያጩን እንደሚደግፍ ያለማሰለስ ምክር ቤቱን ማሳወቁን እንደቀጠለ አመልክተዋል፡፡

“የኔቶን የቅንጅት አሰራር እና የዩናይትድ ስቴትስን ብሔራዊ ጸጥታ ይጠቅማል” ሲሉም ብሊንክን አክለው ገልጸዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ስዊድን እና ፊንላንድ አባል መሆን የሚቃወሙት የህብረቱ አባል ሀገሮች ቱርክ እና ሀንጋሪ ብቻ ሲሆኑ ዩናይትድ ስቴትስ ሁለቱ ሀገሮች በአፋጣኝ ህብረቱ እንዲቀላቀሉ የምትደግፍ መሆኗን ብሊንክን አሳውቀዋል፡፡

ቱርክ በበኩሏ“ በሽብርተኝነት የፈረጅኳቸውን ድርጅቶች አስመልክቶ ከመጠን ያለፈ የላላ አቋም ስለምትከተል ጸጥታዬ ላይ ስጋት ደቅናብኛለች” በማለት የምትከስሳትን ስዊድን የኔቶ አባል መሆን ትቃወማለች፡፡ “ሁሉም ወገኖች ስዊድንን ይህንን ጉዳይ እንድታስተካክል ሊያሳስቡዋት ይገባል” ስትልም ቱርክ ተናግራለች፡፡

በቅርቡ ቱርክን የጎበኙት የኔቶ ዋና ጸሐፊ ዬንስ ስቶልትንበርግ በበኩላቸው “ቱርክ የሁለቱን ሀገሮች አባልነት የምትደግፍበት ወቅቱ አሁን ነው” ብለዋል፡፡

የቱርክ ባለሥልጣናት በበኩላቸው “የስዊድንን እና የፊንላንድን ጉዳይ ለየብቻው እናስተናግደዋለን” ያሉ ሲሆን “ፊንላንድ አባል እንድትሆን ልንፈቅድ እንችል ይሆናል” ሲሉ ጠቁመዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ዩናይትድ ስቴትስ በቅርቡ በከባድ ርዕደ መሬት ለተመቱት ለቱርክ እና ለሶሪያ የ100 ሚሊዮን ዶላር ተጨማሪ እርዳታ ልትሰጥ ቃል ገብታለች፡፡

በሁለቱ ሀገሮች በርዕደ መሬቱ ከ44 ሺህ በላይ ሰዎች ሞተዋል፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ብሊንከን ሀገራቸው ለቱርክ እርዳታ መስጠቷን እንደምትቀጥል ቃል ገብተዋል፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ብሊንክን ከቱርክ በኋላ ወደግሪክ እንደሚጓዙ ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG