በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ብሊንከን እና የኖርዌዩ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ተነጋገሩ


የዩናይትድ ስቴትሱ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንተኒ ብሊንከን
የዩናይትድ ስቴትሱ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንተኒ ብሊንከን

የዩናይትድ ስቴትሱ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንተኒ ብሊንከን እና የኖርዌዩ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ኤስፐን ባርት አይደ ዛሬ ብራስልስ ላይ ኔቶ ዋና መሥሪያ ቤት ውስጥ ተገናኝተው ተወያይተዋል።

ዛሬ ማክሰኞ በዩክሬን ጉዳይ ላይ ላተኮረው የኔቶው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ብራሰልስ የሚገኙት ብሊንከን፣ በነገው ዕለት ወደ ሰሜን መቄዶኒያዋ ስኮፒያ አቅንተው በአውሮፓ የሰላምና የደህንነት ድርጅት ጉባኤ ላይ ይሳተፋሉ።

ብሊንከን፣ በሳምንቱ መገባደጂያም ዩናይትድ ስቴትስ በጋዛ የተደረሰው ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ስምምነት የሚራዘምበትንና ተጨማሪ ታጋቾች የሚለቀቁበትን መንገድ ለማፈላለግ ተስፋ ለጣለችበት ውጥኗ ወደ የመካከለኛው ምስራቅ እንደሚመለሱ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር አስታውቋል። ብሊንከን የእስራኤል እና የሐማስ ጦርነት ከጀመረች ወዲህ ወደ አካባቢው ሲጓዙም ያሁኑ ሶስተኛቸው ይሆናል።

እስራኤል በመስከረም 26ቱ ጥቃት ወቅት በሐማስ ተጠልፈው የተወሰዱ ታጋቾች የሚለቀቁበትን ሁኔታ እንዲፈጠር ስትል ወታደራዊ እንቅስቃሴዋን ለመግታት መስማማቷ ይታወቃል። ትላንት ከማብቃቱ በፊት ለተጨማሪ ሁለት ቀናት የተራዘመው ስምምነት፣ እንደገና ካልተራዘመ በስተቀር፣ ብሊንከን እስራኤል በሚገቡበት ወቅት የተፈጻሚነት ጊዜው ያበቃል።

የዋይት ሀውስ የብሄራዊ ደህንነት ምክር ቤት ቃል አቀባይ ጃን ኪርቢ ትላንት ሰኞ በሰጡት አስተያየት፣ አገራቸው ጊዜያዊው የተኩስ አቁም ስምምነቱ ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ ተራዘሞ የማየት ተስፋ ማሳደሯን፣ ይሁንና ይህም ሐማስ ታጋቾችን መልቀቁን በሚቀጥልበት ሁኔታ ላይ እንደሚወሰን ተናግረዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG