በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ብሊንከን በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኙ የህንድ የንግድ አመራሮች አነጋገሩ


የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን፣ ሰኞ እለት ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው ኔንዊክ ጋለሪ በተካሄደው 48ኛ የዩናይትድ ስቴትስ እና ህንድ የንግድ ጉባዔ ላይ ተገኝተው ንግግር አድርገዋል።

ብሊንከን በንግግራቸው በህንድ እና በዩናይትድ ስቴትስ መካከል፣ በተለይ በጤና፣ ደህንነት፣ ኢኮኖሚ፣ ፈጠራ እና በሁለቱ ሀገራት ህዝቦች መካከል ልዩ ግንኙነት መኖሩን አፅንኦት ሰጥተዋል።

"እዚህ የተሰበሰብነው፣ ታሪካዊ እንደሆነ በምናምነው የጠቅላይ ሚኒስትር ሞዲ ጉብኝት ዋዜማ ላይ ነው" ያሉት ብሊንከን፣ በዓለም አንጋፋ እና ትልቅ የሆኑት ሁለቱ ዲሞክራሲዎች ለዜጎቻቸው ለመድረስ እና ለማብቃት የሚችሉ መንግስታት መሆናቸውን የማሳየት ግዴታ እንዳለባቸው ተናግረዋል።

ክልላዊ እና ዓለም አቀፋዊ ተግዳሮቶችን ለመፍታት የጋራ ትብብር እና ቁርጠኝነት አስፈላጊ መሆኑን አስምረውም፣ የሕንድ ውቅያኖስንና የፓስፊክ ውቅያኖስን በሚያገናኘው [ኢንዶ -ፓስፊክ] አካባቢ ነፃ፣ ክፍት፣ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ሰዎች እና ቁሳቁሶች እንዲሁም ሀሳቦች በነፃነት እና ህጎች በትክክል በሚተገበሩበት መንገድ መተላለፍ የሚችሉበት መንገድ ሆኖ ለመገንባት የሁለቱ ሀገራት ትስስር ወሳኝ ነው ብለዋል።

ብሊንከን እንደ ጉግል፣ ማስተር ካርድ እና የዓለም ባንክን የመሳሰሉ የአሜሪካ ግዙፍ ተቋማት አመራሮች ህንዳዊ አሜሪካውያን መሆናቸውን አስታውሰው፣ የዩናይትድ ስቴትስ እና የህንድ የትምህርት ስርዓቶች ታላላቅ መሪዎችን ማፍራታቸውን አመልክተዋል።

XS
SM
MD
LG