በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሶማሊያ ሞቃዲሾ ፍንዳታ አራት ሰዎች ሲገደሉ ሥድስት ሰዎች ቆስለዋል

ሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ አቅራቢያ ዛሬ ማክሰኞ በርቀት መቆጣጠሪያ በፈነዳ ቦምብ አራት ሰዎች ሲገደሉ ሌሎች ሥድስት ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን ባለሥልጣናትና እማኞች ገለፁ።

ሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ አቅራቢያ ዛሬ ማክሰኞ በርቀት መቆጣጠሪያ በፈነዳ ቦምብ አራት ሰዎች ሲገደሉ ሌሎች ሥድስት ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን ባለሥልጣናትና እማኞች ገለፁ።

ሞቃዲሾ ዳርቻ ላይ በሚገኝ የመኖሪያ አካባቢ አንድ ወታደራዊ ተሽከርካሪ ላይ በደረሰው የፈንጂ ጥቃት ሦስት ወታደሮችና አንድ የሰባት ዓመት ልጅ መገደሉን እማኞች ገልፀዋል። ልጁ መንገድ ዳር ቆሞ የነበረ መሆኑን አክለዋል ። ጽንፈኛው ቡድን አልሻባብ ፍንዳታውን ያደረስኩ እኔ ነኝ ሲል ኃላፊነት ወስዷል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG