በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአንጥረኛነት ፈተና በትግራይ


የአንጥረኛነት ፈተና በትግራይ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:20 0:00

የአንጥረኛነት ፈተና በትግራይ

በትግራይ ክልል በባህላዊ የብረታብረት መገልገያ ዕቃዎች እና ጌጣጌጦች ሥራ ላይ የተሰማሩ የጥበበ እድ ሞያተኞች፣ እየደረሰብን ነው ባሉት ማኅበራዊ መገለልና ጥቃት የተነሣ፣ ልጆቻቸው ከትምህርት ገበታ እየራቁ መኾናቸው በእጅጉ እንዳሳሰባቸው ገልጸዋል።

በየጊዜው እየከፋ መምጣቱን በገለጹት ጥቃት ለተፈናቃይነት መዳረጋቸውን የተናገሩት የእጅ ጥበብ ሞያተኞቹ፣ "አስነዋሪ" ሲሉ በገለጹት አኳኋን ግድያ የተፈጸመባቸው የቤተሰቦቻቸው አባላት መኖራቸውን ለአሜሪካ ድምፅ አስረድተዋል።

መብቶቻቸውን በሕግ ለማስከበር ጥረት ቢያደርጉም "ምስክር አቅርቡ" በሚል ፍትሕ ለማግኘት አለመቻላቸውን ሞያተኞቹ አመልክተዋል። "መምህራን፣ ካህናት እና ፖሊስ አመለካከታቸው ቢስተካከል እኛም እንደ ሰው እንኖር ነበር፤” ሲሉም መፍትሔው የአመለካከት ለውጥ እንደኾነ ጠቁመዋል።

የእጅ ባለሞያዎቹ ይደርስብናል ያሉትን በደል ለመከላከልና ሲበደሉም ፍትሕ ርትዕ እንዲያገኙ የሚያግዝ፦ "የትግራይ የእደ ጥበብ ባለሞያዎች ማኅበር" የተሰኘ የመብቶች ተሟጋች ማቋቋማቸውንም አክለው አስታውቀዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG