አዲስ አበባ —
የኢትዮጵያ ፓርላማ ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳን የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ አድርጎ ሾማቸው፡፡ ተሿሚዋን በዕጩነት ያቀረቧቸው ጠ/ሚኒስትር አብይ አሕመድ የሚቀጥለው ሀገር አቀፍ ምርጫ ኢትዮጵያ ለዕውነተኛ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት መሰረት የሚጣልበት ክንውን እንደሚሆን ተናገሩ፡፡ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ለዚህ ዴሞክራሲያዊ ምርጫ በአንድ ልብ እንዲነሳም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ