በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ብርትኳን ሚደቅሣ ስለሕገወጥ እሥራት


በሕገወጥ እሥራት ላይ ከአሜሪካ ድምፅ ጋር የተደረገ የወ/ት ብርትኳን ሚደቅሳ ቃለ-ምልልስ፡-

በመንግሥታት የሚፈፀሙ ሕገወጥ እሥራቶችን የሚከታተለው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ጥበቃ ኮሚቴ የተመሠረተበትን ሃያኛ ዓመት ባለፈው ሣምንት ሰኞ፤ ኅዳር 4 ቀን 2004 ዓ.ም ፓሪስ ከተማ ውስጥ አክብሯል።

በሥነሥርዓቱ ላይ ተገኝተው ተሞክሯቸውን እንዲያጋሩ ሦስት የቀድሞ የእሥር ሰለባዎች ተጋብዘው እንደነበር ሲዘገብ እነርሡም ከሚያንማር ወይም በርማ የዴሞክራሲ እንቅስቃሴ መሪና ለሰላም የኖቤል ተሸላሚዋ አንግ ሣን ሱ ኪ፣ ኢትዮጵያዊቷ ዳኛና የፖለቲካ መሪ ብርትኳን ሚደቅሳ፣ እንዲሁም ሦሪያዊው ዳኛና የሰብዓዊ መብቶች ታጋይ ሃይጠም አልማሌኽ ናቸው።

ወይዘሪት ብርትኳን ሚደቅሳ በወቅቱ የሕግን አግባብ ያልተከተለ እሥራት ለሚከታተለው የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚቴ ያደረጉትን ንግግር ለእኛም እንዲያጋሩ «የዲሞክራሲ በተግባር» ፕሮግራም እንግዳ አርገናቸዋል።

ከአዘጋጁ ሰሎሞን ክፍሌ ጋር ያደረጉትን ቃለ ምልልስ ያዳምጡ።

XS
SM
MD
LG