በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የወይዘሪት ብርቱካን ይቅርታና እስር አንድምታ


ሁለት ዓመታት ከተቃረበ እስር በኋላ በቅርቡ የተለቀቁት የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ሊቀ መንበር ወ/ሪት ብርቱካን «ይቅርታ፥» - የእስር የተለቀቁበት ሁኔታና የእስር ቤት ቆይታ እያነጋገረ ነው።

የውይይቱን የመጀመሪያ ክፍል ለማድመጥ እዚህ ይጫኑ።

ለመሆኑ የወ/ሪት ብርቱካን ከእስር መለቀቅ፥ አፈታታቸውና «ይቅርታው» በቀጣዩ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ሂደት ምን ዓይነት አንድምታ ይኖረው ይሆን? ምንስ ዓይነት አቀባበልና ትርጓሜ ተሰጠው? በሚሉትና ተያያዥ ጥያቄዎች ዙሪያ የተካሄደ ውይይት ነው።

የውይይቱ ተሳታፊዎች፥ በCalifornia State University የፖለቲካ ሳይንስ መምህርና የህግ ባለ ሞያው ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረ ማርያም፥ አቶ እስክንድር ነጋ፥ በሰርክ ዓለም አሳታሚ ስር ይታተሙ የነበሩትት፥ የሚኒሊክ፥ አስኳልና ሳተናው ጋዜጦች ዋና አዘጋጅ ከአዲስ አበባ፤ እንዲሁም «ወ/ሪት ብርቱካን ነፃ ይለቀቁ፤» በእንሊዝኛው “Free Birtukan” በሚል መጠሪያ በተለያዩ አገሮችና ልዩ-ልዩ የዩናይትድ ስቴትስ ግዛቶች ወ/ሪት ብርቱካን እንዲለቀቁ ሲያደርግ በቆየው እንቅስቃሴ የሚታወቀው ቡድን አባል፤ ወጣት ስሂን ኃይሌ ናቸው።

የቀደሙት ሁለት ተወያዮች የወ/ሪት ብርቱካንን መፈታትን ተከትሎ የፃፏቸውን ጨምሮ፤ በርዕሰ ጉዳዩ ላይ በሥፋት ፅፈዋል።

የውይይቱን ሁለተኛ ክፍል ለመስማት ማጫወቻውን ይጫኑ።

XS
SM
MD
LG