በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“ማንም ሰው ማድረግ ከሚችለው ነገር ወደ ኋላ የሚልበት ጊዜ አይደለም”- ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ


ወ/ት ብርቱካን ሚዴቅሳ በ2004 ዓ.ም ከእስር ሲፈቱ
ወ/ት ብርቱካን ሚዴቅሳ በ2004 ዓ.ም ከእስር ሲፈቱ

የቀድሞዋ የተቃዋሚ መሪ ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ወደ ኢትዮጵያ ተመለሱ። ነገ ጠዋት አዲስ አበባ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል።

“አገሪቱ ባለችበት ሁኔታ ለመርዳት ማንም ሰው የሚችለውን ነገር ለማድረግ ወደ ኋላ የሚልበት ጊዜ አለመሆኑን በመረዳት እኔም በበኩሌ ባለኝ አቅም፣ በሞያዬ፣ በልምድና በዕውቀቴ የምችለውን ለማዋጣት እና ያም ምን እንደሚሆን ለመወያየት ነው የምሄደው። በጣም ጥሩ ቀን ነው ለእኔ።” ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ።

“ወደ አገራቸው ተመልሰው በሕግም ሆነ በሌሎች ጉዳዮች ለአገሪቱም ለሕዝቡም ባላቸው ዕውቀትና ልምድ አስተዋጾ ማበርከት ፈልገው መምጣታቸው የሚያስመሰግናቸው ነው። እኛም አብረናቸው ለመስራት ዝግጁ ነን።” የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ አቶ ብርሃኑ ጸጋዬ

በኢትዮጵያ የተጀመረውን የዲሞክራሲ እንቅስቃሴ ለማገዝ ታልሞ የተፈጠረው ዕድል ያበረታታቸው መሆኑን የቀድሞዋ የቅንጅት አመራር አባልና የአንድነት መሪ ወይዘሪት ብርቱካን ዛሬ ወደ አዲስ አበባ ከመብረራቸው አስቀድሞ በተለይ ለአሜሪካ ድምጽ በሰጡት ቃል ገለጡ።

የፌድራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ አቶ ብርሃኑ ጸጋዬ በኩላቸው የወይዘሪት ብርቱካንን ወደ ሃገር መመልስ አስመልክቶ በሰጡት አስተያየት “በአገሪቱ በሚካሄደው እንቅስቃሴ እንዲያግዙ እንፈልጋለን። አብረናቸው ለመስራትም ዝግጁ ነን።” ብለዋል።

(ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)

“ማንም ሰው ማድረግ ከሚችለው ነገር ወደ ኋላ የሚልበት ጊዜ አይደለም” - ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:06 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG