በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በቲዩቢንገን ከተማ (ጀርመን) ለብርቱኳን ሚደቅሳ የተዘጋጀ የሩጫ ውድድር


ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ እንድትፈታ ግፊት ለማድርግ በቲዩቢንገን እሁድ ዕለት የሩጫ ውድድር እና ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄዷል።

ለወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ በተዘጋጀው የሩጫ ውድድር ላይ ወደ 2700 ሯጮች መሳተፋቸው በተነገረበት ሥነ ሥርዓት ቁጥራቸው 25,000 የሚደርስ ሰዎች መገኘታቸውን አዘጋጆቹ ይናገራሉ።

የአንድነት ለፍትህና ዲሞክራሲ ፓርቲ መሪ ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ከእስር መለቀቅ በመጠየቅ ሥነ ሥርዓቱን የጠራው መቀመጫውን በጀርመን ያደረገውና የኢትዮጵያውያን የመብት ተሟጋች ድርጅት የተባለው ቡድን የከተማው ማዘጋጃ ቤት ተጠሪዎችና የኦሎምፒኩን ኮከብ ጨምሮ በርካታ ጀርመናውያን የቡድኑን ጥሪ በመደገፍ ተገኝተዋል።

ዝግጅቱ ከመካሄዱ በፊት በጀርመኑ የኢትዮጵያውያን ሰብዕዊ መብት ኮሚቴ ተጠሪ አቶ ስዩም ሀብተማሪያም ጋር የተደረገውን ዘገባ ያድምጡ።

ተመሳሳይ ርእስ

XS
SM
MD
LG