በኢትዮጵያ ለሚካሄድ የመጠጥ ውሀ ፕሮጀክት ገንዘብ ለማሰባሰብ የ 12,000 ኪሎሜትር የቢስክሌት ጉዞ የጀመሩት ካናዳዊ በጎ አድራጊ ማይክል ፖል እስካሁን ባለው ጊዜ ከአንድ ሚልዮን ብር በላይ ማሰባሰባቸውን አስታውቀዋል።
በካናዳ ኤድመንተን የሚኖሩት የ55 አመት እድሜ የሆኑት በጎ አድራጊ ከካይሮ እስከ ኬፕታውን በብስኪሌት በመጓዝ ነው በቦንኬ ኢትዮጵያ ላሉት ሰዎች ንጹህ የመጠጥ ወሀ ለማስገባት የሚደረገውን ጥረት ለመርዳት የወሰኑት። እስካሁን ባለው ጊዜ ከግብጽ ወደ ሱዳን ከሱዳን ደግሞ ወደ ኢትዮጵያ ተጉዘዋል።