በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባይደንና ጂንፒንግ ነገ ይገናኛሉ


ፎቶ ፋይል፦ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደንና የቻይናው መሪ ሺ ጂፒንግ
ፎቶ ፋይል፦ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደንና የቻይናው መሪ ሺ ጂፒንግ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደንና የቻይናው መሪ ሺ ጂፒንግ ነገ ሃሙስ እንደሚነጋገሩ የአሜሪካ ባለሥልጣናትን የጠቀሱ የዜና ማሠራጫዎች ዘግበዋል።

ቻይና ታይዋይንን አስመልክቶ በምታነሳው የይገባኛል ጥያቄ ዙሪያ በዋሽንግተንና በቤጂኒግ መካከል አዲስ ውጥረት በበረታበት በዚህ ወቅት ሁለቱ መሪዎች የሚገናኙት በአራት ወር ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑ ነው።

የዩናይትድ ስቴትስ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ ናንሲ ፐሎሲ በቅርቡ ታይዋንን እንደሚጎበኙ የተዘገበ ሲሆን ጉብኝቱን እንዳያደርጉ ቻይና አስጠንቅቃለች።

አፈጉባኤዋ ታይዋንን ቢጎበኙ ዋሽንግተን “የሚያስክተለውን መዘዝ ትሸከማለች” ብላለች ቻይና ረቡዕ ባወጣችው መግለጫ።

ፐሎሲ ታይዋንን የሚጎበኙ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ባይሰጡትም ራስ ገዟን ደሴት እንደሚገበኙ ዘገባዎች ያመለከቱት በዚህ ወር ውስጥ እንደነበር ይታወሳል።

XS
SM
MD
LG