በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዌስት ባንክ የሚገኙት ባይደን ለእስራኤልና ፍልስጤማውያን ሰላም እንደሚሰሩ ተናገሩ


የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ከፍልስጤም መሪ መሃሙድ አባስ ጋር ዌስት ባንክ ቤተልሔም እአአ ሐምሌ 15/2022
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ከፍልስጤም መሪ መሃሙድ አባስ ጋር ዌስት ባንክ ቤተልሔም እአአ ሐምሌ 15/2022

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ከፍልስጤም መሪ መሃሙድ አባስ ጋር ዌስት ባንክ ውስጥ ዛሬ አርብ ተገናኝተዋል፡፡ ባይደን ምንም እንኳ ገና ረጅም ርቀት የሚቀረው መምሰሉን ቢያምኑም፣ ለእሥራኤል ፍልስጤም ችግር የሁለት መንግሥታት ምሥረታ መፍትኄ ላይ እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡

“ፍስልጤማውያን አሁን እየተጎዱ ነው” ያሉት ባይደን “ያ ሊሰማችሁ ይችላል፡፡ ሀዘናችሁና ብስጭት አላችሁ፡፡ ዩናይትድ ስቴትስም ውስጥም ያ ስሜታችሁ ሊሰማን ይችላል” ብለዋል፡፡

ባይደን የቀጥታ ድርድር እንደገና መጀመር ያለበት መሆኑን ገልጸው፣ ያ የፍልስጤማውያን መንግሥት እና የእስራኤል መንግሥት ተመስርቶ ጎን ለጎን ሁለቱም አገሮች በወሰኖቻቸው ውስጥ በሰላምና ደህንነታቸው ተጠብቆ ሊኖሩ ይችላሉ ብለዋል፡፡

ባይደን አያዘውም “ፍልስጤማውያን ነጻ፣ ሉዐላዊ፣ ፋይዳና የራሱ አዋስኝ የወሰን ክልል ያለው፣ የራሳቸው መንግሥት መመስረት ይችላሉ፡፡ በዚህች ምድር ጥንታዊ ትስስር ያላቸው በሰላምና ደህንነት መኖር የሚችሉበት የሁለት መንግሥታት ምሥረታ ለሁለት ህዝቦች ያስፈልጋል” ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የፍልስጤሙ መሪ አባስ በበኩላቸው “በእስራኤል የተወረረውን መሬታችንን ሁኔታ ለመቀየር ጊዜው አሁን ነው” በማለት እስራኤል“ከህግ በላይ የሆነች መንግስት ሆና መቀጠል አትችልም” ብለዋል፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ ለፍልስጤማውያን የ316 ሚሊዮን የገንዘብ እርዳታ እንደምትሰጥ ባይደን በጉብኝታቸው ወቅት ያስታወቁ ሲሆን በምስራቅ ኢየሩሳሌም ያሉትን ሆስፒታሎች ጨምሮ ለምጣኔ ሀብቱ ጠቃሚ በሆነው የገንዘብ እርዳታ ዙሪያ ይመክራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተመልክቷል፡፡

ባይደን በአካባቢው የሚገኙ የፍልስጤማውያንን የበርካታ ዓመታት የጤና አገልግሎት ተቋማት ለመደገፍ የታለመውን የ100 ሚሊዮን ዶላር የገንዘብ እርዳታ ይፋ እንደሚያደርጉ ተነግሯል፡፡

“እነዚህ ሆስፒታሎች ለፍልስጤማውያን የጤና ሥርዓት የጀርባ አጥንት ናቸው” በማለት የነርሶቹን ሥራ ያደነቁት ባይደን፣ የአስችኳይ ህክምና እርዳታ አስፈላጊነትና ጥቅምን በተመለከተ የራሳቸውን ቤተሰብ ልምድ ጠቅሰው ተናግረዋል፡፡

በይፋ ይገለጻሉ ተብለው ከታቀዱት መካከል በጋዛና በዌስት ባንክ ይዘረጋሉ የተባሉት የ4ጂ የገመድ አልባ (ዋየርለስ) መስመሮችን ጨምሮ በፍልስጤማውያን ኢኮኖሚ ልማት ላይ የሚያተኩሩ የልማት እቅዶች ይገኙበታል፡፡

ባይደን ከዚህ በመቀጠል ወደ ሳኡዲ አረብያ እንደሚያመሩ ተመልክቷል፡፡ ባይደን በሳውዲ አረብያ ይደርሳሉ ተብሎ ከተጠበቀበት ጥቂት ሰዓታት ቀደም ብሎ ሳኡዲ አረብያ ሀሙስ ምሽቱ ላይ የአየር ክልሏን “ለሁሉም አገር በረራዎች” ክፍት በማድረጓ ከእስራኤል ወይም ወደ እስራኤል የሚደረጉ በረራዎች ላይ የተጣለው እገዳ እንዲያበቃ ያደርጋል ተብሏል፡፡

ትናትን ሀሙስ ባይደን ከእስራኤል ተጠባባቂ ጠቅላይ ሚኒስትር ያኢር ላፒድ ጋር ተገናኝተዋል፡፡ ከስብሰባቸው በኋላ ሁለቱ መሪዎች በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ኢራን የኒውክለር ኃይል ባለቤት እንዳትሆን የማይፈቅዱ መሆኑን እንደተስማሙበት አስታውቀዋል፡፡

XS
SM
MD
LG