በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባይደን ግሽበቱን መዋጋት ቀዳሚ አጀንዳቸው መሆኑን አስታወቁ


ፎቶ ፋይል፦ የነዳጅ ዋጋ
ፎቶ ፋይል፦ የነዳጅ ዋጋ

ዩናትይድ ስቴትስ ውስጥ እየተቃረበ በመጣው የመካከለኛው አጋማሽ ምርጫ፣ ግሽበት ቁልፍ የፖለቲካ መነጋገሪያ ሆኗል፡፡ ፕሬዚዳንት ባይደን ለግሽበቱ አብዛኛውን ድርሻ የሚይዘው የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ዩክሬንን በመውረራቸው ምክንያት በዓለም የተፈጠረው የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ መሆኑን ይገልጻሉ፡፡

ባይደን ዴሞክራቲክ ፓርቲያቸው ግሽበትን በ8.5 ከመቶ በመቀነስ የምጣኔ ሀብት ጽንፈኞች ካሏቸው ተዋሚዎቻቸው የተሻለ እቅድ ያለው መሆኑንም ገልጸዋል፡፡ የዋጋ ግሽበትን ለመረዳት የምጣኔ ሀብት ባለሙያዋ መሆን አያስፈልግም፡፡ ለአብዛኞቹ አሜሪካውያን ከምግብ አነስቶ እስከ ነዳጅ ድረስ ሁሉንም ነገር መጨመሩን በቅርብ እያዩት ነው፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በመጭው ህዳር ለመራጮች ይህ ትልቅ መነጋገሪያ መሆኑን ያውቃሉ፡፡ እንዲህ አሉ “እያንዳንዱ አሜሪካዊ እንዲያውቅ የምፈልገው ግሽበት ትልቅ ትኩረት ሰጥቼ የምከታተለውና ቅድሚያ የሰጠሁት የአገር ውስጥ ጉዳይ መሆኑን ነው” ባይደን በተዘዋወሩባቸውና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሚዋዥቁ ቁልፍ የምርጫ ክፍለ ግዛቶች፣ እንደ ኖርዝ ካሮላይና፣ ኦሃዮ፣ አይዋና አላባማ፣ በመሳሰሉት፣ ትልቁ ርዕሰ ጉዳያቸው ያደረጉት ምጣኔ ሀብቱን ነው፡፡

አሁን የተሰበሰበው የህዝብ አስተያየት እንደሚያሳየው፣ የባይደን ምጣኔ ሀብት አያያዝ፣ ከ40 ከመቶ በላይ በሆኑ አሜሪካውያን ብቻ የተደገፈ ሲሆን፣ የሪፐብሊካን ተችዎቻቸውም የሚምሯቸው አልሆኑም፡፡ ሪፐብሊካኑ የህግ መወሰኛው ምክር ቤት አባል ሪክ ሳንትሮም እንዲህ ብለዋል “ሪፐብኪላንን ከማጥቃት ውጭ ምን ነገር እያደረጉ አይደለም፡፡ በአሁኑ ወቅት ግሽበትን አሰመልክቶ አንድ ነገር ማድረግ ከፈለጉ ማድረግ ያለባቸው ሥልጣናቸውን መልቀቅ ነው፡፡

እሳቸው ወደ ሥልጣን ከመጡበት ጊዜ ጀምሮ ባሉት ወራት የግሽበቱ ሁኔታ ተባብሷል፡፡” ባይደን በዚህ አይስማሙም፡፡ አሁን በቅርቡ ምጣኔ ሀብቱን የሚያነቃቃ ነገር ማድረጋቸውን ይገልጻሉ፡፡ የኢንተርኔት ተደራሽነትን ለመጨመር የአገልግሎት ዋጋውን ቀንሰዋል፣ ከመጠባበቂያው የነዳጅ ክምችት ተጨማሪ ነዳጅ ለቀዋል፣ ለጋዝና ኤታኖል አቅርቦት በ15 ከመቶ እንዲስፋፋ አድርገዋል፡፡

ባይደን ግሽበቱን መዋጋት ቀዳሚ አጀንዳቸው መሆኑን አስታወቁ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:02 0:00

ባይደን ስለተቃዋሚዎቻቸው ይህን ብለዋል “የህግ መወሰኛው ምክር ቤት አባል የሆኑት ሩፐብሊካኑ ሴነተር ሪክ ስካት ትልቅና ጥቅል የሆነውን አጀንዳቸውን በግልጽ አስቀመውጠታል፡፡

አጀንዳቸው 75 ሚሊዮን በሚሆኑና የዓመት ገቢያቸው ከ100ሺ ዶላር በታች በሆኑ 95 ከመቶው አሜሪካውያን ቤተሰቦች ላይ ታክስ መጨመር ነው፡፡ በአማካይ የሚጨምሩት ታክስ በቤተሰብ 1ሺ500 ዶላር ነው፡፡ እንደኔ አስተያየት እንደገና ወደ ኋላ የተመለሱ ይመስለኛል፡፡”

ዋይት ኃውስ ምጣኔ ሀብቱን ሂደት ያቋረጠውን የኮቪድ 19 ወረርሽኝ፣ የነዳጅና የሰብል እህል ዋጋን ከፍ ያደረገውን የፕሬዚዳንት ፑቲንን የዩክሬን ወረራ ተጠያቂ ያደርጋሉ፡፡ ይሁን እንጂ ተንታኞች ባይደን ከህዳሩ ምርጫ በፊት ሁኔታዎችን ወደሳቸው ለመሳብ በቂ ጊዜ የላቸውም ይላሉ፡፡

ከብሩኪንግ ተቋም ቢል ጋልስተን ይህን ብለዋል “መሠረታዊ የፖሊሲ ለውጥ በጊዜ ሂደት ውስጥ ለውጥ ያመጣል፡፡ ጥያቄው ግን ከአሁን ጀምሮ የመካከለኛው አጋማሽ ምርጫ እስኪካሄድ ድረስ ለውጥ ማምጣት ከቻሉ ነው፡፡ ያንን ተግባራዊ ለማድረግ ፕሬዚዳንቱ በጣም እድለኛ መሆን አለባቸው፡፡” ተንታኞች የዩናይትድ ስቴትስ ግሽበት ተጽኖውን በዓለም አቀፍ ደረጃ ማሳረፉን ይገልጻሉ፡፡

ትናንት ማክሰኞ የዓለም ሠራተኞች ድርጅት እኤአ ባለፈው መጋቢት፣ ዓለም አቀፉ ግሽበት በ9.2 ከመቶ መጨመሩን አስታውቋል፡፡ ይህ ቀደም ሲል ከነበረው የመጋቢት 2021፣ በ3.7 ከመቶ መጨመሩን ያሳያል፡፡

ከአሜሪካ ኢንተርፕራይዝ ተቋም ዴዝሞንድ ላችማን እንዲህ ብለዋል “ይህ ግሽበት የሚያስከትለው ነገር ቢኖር በበለጸጉ የቡድን 7 አገሮች የምጣኔ ሀብት ውድቀትን ነው፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ፣ ያ ለመላው ዓለም ምጣኔ ሀብት ጥሩ ነገር አይደለም፡፡”

በአጠቃላይ ይህ ችግር በአሜሪካ መራጮች ላይ አርፏል፡፡ መካከለኛው አጋማሽ ምርጫ 39 በሚደርሱ የአሜሪካ ክፍለ ግዛቶች ሁሉንም 435 የተወካዮች ምክር ቤት ወንበሮችና አንድ ሶስተኛ የሆኑትን የህግ መወሰኛው ምክር ቤት መቀመጫዎችን ለፍልሚያ አቅርቧቸዋል፡፡

XS
SM
MD
LG